“በስደት መኖር ስለማይቻል እንዲኹም ሀገር ለቅቆ የትም ስለማይደረስ ጠላትን በርትታችሁ ልትታገሉ ይገባል” በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ካሊፎርንያ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መምህር ሀብተማሪያም እማኛው

150
ደባርቅ፡ ጥቅምት 22/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ካሊፎርንያ ሀገረ ስብከት በወቅታዊ ሀገራዊ ችግር ለተፈናቀሉ ወገኖች 1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የምግብ ድጋፍ አድርጋለች።
በአሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ቡድን ምክንያት ከቀያቸው ተፈናቅለው በደባርቅ ከተማ የተገኙት አበባው መንግሥቱ በየወቅቱ ለሚደረግላቸው ድጋፍ በማድነቅ አመስግነዋል። “ተፈናቃይ ወጣቶች ዘመቻውን በመቀላቀል ለስደት የዳረጋቸውን ጠላት መደምሰስ ይኖርባቸዋል” ብለዋል።
እናኑ መሥፍን የተባሉት ተፈናቃይ በተለይ ዛሬ ለተበረከተላቸው ድጋፍ ብቻ ሳይኾን ባገኙት መንፈሳዊ ትምህርትና ምክር የሥነ ልቦና ጥንካሬ እንደተሰማቸው ተናግረዋል። መንግሥት ተፈናቃዮችን አደራጅቶ ለትግል እንዲያበቃም ጠይቀዋል።
ደባርቅ በመገኘት ድጋፉን ያበረከቱት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ካሊፎርንያ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ መምህር ሀብተማሪያም እማኛው “በስደት መኖር ስለማይቻልእንዲኹም ሀገር ለቅቆ የትም ስለማይደረስ ጠላትን በርትታችሁ ልትታገሉ ይገባል። በተለይ እናንተ ወጣቶች አካባቢያችሁን ለቅቃችሁ ወዴት ነው የምትሰደዱት? እናንተ ታግላችሁ ወገኖቻችሁን ማስከበር ይኖርባችኋል እንጂ መሰደድ የለባችሁም” ነው ያሉት።
በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ ወገኖቻችሁም ከጎናችሁ ናቸው ብለዋል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ካሊፎርንያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ በርናባስ፣ እናንተ በግፈኞች የተሰደዳችሁ ወገኖች ወገኖቻችሁ ደጀን ስለሆኑላችሁ ደስታ ሊሰማችሁ ይገባል ነው ያሉት።
በሀገር ውስጥም ኾነ በውጭ የሚኖሩ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ስለሚደግፏችሁ ጥንካሬ ሊሰማችሁ ይገባል ብለዋል።
የሰሜን ጎንደር ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሠላምይሁን ሙላት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ ካሊፎርንያ ሀገረ ስብከት ላደረገው ድጋፍም አመስግነዋል። በክተት አዋጁ መሠረት ተፈናቃይ ወጣቶችና ለትግል ብቁ የኾኑትን ጀግኖች በማደራጀት ወደትግሉ የሚገቡበት አሠራር እየተሠራ ነው ብለዋል።
ተፈናቃዮችም ቢኾኑ ለትግል ዝግጁ መሆናቸውን ኃላፊው ገልጸዋል።
በዞኑ አሸባሪው ቡድን ባደረገው ወረራ 135 ሺህ በላይ ወገኖችተፈናቅለው እንደሚገኙ ከተጠሪ ጽሕፈት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ- ከደባርቅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article‟ለትግል ብቁ የኾነውን ኹሉ ወደ ግንባር እያንቀሳቀስን ነው“ የደባርቅ ወረዳ
Next articleደቡብ ጎንደር ዞን ሕዝባዊ ማዕበሉን በፍጥነት ማደራጀት ጀምሯል፡፡