የአማራ ክልል መንግሥት ያስተላለፈውን የክተት ጥሪ የተቀበሉ የፋኖ እና የሚሊሻ አባላት አሸባሪውና ወራሪዉ የትግራይ ኃይልን ግብዓተ መሬት እስኪፈጸም ድረስ ለመፋለም ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ፡፡

351

ጎንደር: ጥቅምት 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል መንግሥት ያስተላለፈውን የክተት ጥሪ ተከትሎ ከጎንደር ከተማ የሚሊሻና የፋኖ አባላት ለዘመቻ ከተዋል።

የክተት ጥሪውን ተቀብለው ከተዉ ያገኘናቸው የፋኖ አባላት መካከል ዓባይ ማንደፍሮ እና ግልገል አንዳርጋቸው መስዋእትነት ከፍለው ሀገራቸውንና ወገናቸዉን ከአረመኔዉ የትህነግ ቡድን ለመታደግ ዝግጁ መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡

ሌላዋ ከታ ያገኘናት የሚሊሻ አባል አፀደ ይግዛዉ በበኩሏ በተወረሩ በተያዙ የክልሉ አካባቢዎች የሽብር ቡድኑ በእናቶች፣ በህጻናት፣ በአዛዉንቶችና በእንስሳቶች ሳይቀር እያደረሰ ያለው ግፍ እንዳስቆጫት ገልጻለች። ይህንን ወራሪ ኃይል ለመመከት ማንኛውንም መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኗን ተናግራለች፡፡

እድሜ እና አካላዊ ብቃቱ የፈቀደለት ዜጋ ሁሉ የክተት ጥሪውን ተቀብሎ ወራሪዉን ባንዳ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት እንዲዘምት ጠይቀዋል፡፡

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ክንቲባ ዘውዱ ማለደ የሕልውና ዘመቻውን ሕዝባዊ ማድረግ ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ መሆኑንም ገልጸዋል።

አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ኃይል አማራን ለማጥፋት እና ለማዋረድ በሕዝባዊ ማዕበል የፈጸመወን ወረራ ለመመከት ሁሉም ዜጋ እንዲዘምት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዘጋቢ:- ይርጉ ፋንታ – ከጎንደር

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleአሸባሪው የህወሓት ቡድን ኢትዮጵያን ለማፍረስ ጥቃት የፈፀመበት ጥቅምት 24 ቀን በልዩ ሁኔታ ታስቦ እንደሚውል መንግሥት አስታወቀ።
Next articleአሸባሪውን መንጋና ተላላኪዎቹን በጋራ ክንድ እንዋጋ!