
ዕለቱ “አልረሳውም እኔም የኢትዮጵያ ሠራዊት ነኝ” በሚል መሪ ሐሳብ ታስቦ እንደሚውል ተገልጿል።
አዲስ አበባ: ጥቅምት 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ደሲሳ የጥቅምት 24ቱን ጥቃት መታሰቢያ አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።
አሸባሪው የህወሓት ቡድን ከ27 ዓመታት ግፍ በኋላ መቀሌ በመመሸግ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ወታደራዊ አሻጥሮችን ሲፈጽም ቆይቷል።
ጥቅምት 24 /2013 ዓ.ም ሀገሩን ለውጭ ጠላት አሳልፎ ለመስጠት ከ20 ዓመታት በላይ ለትግራይ ሕዝብ ጠባቂ የነበረውን የሰሜን ዕዝ ሠራዊት በማጥቃት ክህደት ፈፅሟል።
ሚኒስትር ዴኤታው ዕለቱ በሠራዊቱ ላይ ጥቃት የተፈጸመበትና የሀገሪቷን ከባድ መሳሪያ ያዘነበ ነበር ብለዋል።
በጥቃቱ ብርቅዬ ጀግኖች በግፍ ተገድለዋል፣ ከባድ መሳሪያዎች ተዘርፈዋል፣ መኮንኖች ታግተዋል፣ ከፍተኛ ጥፋትም ተፈፅሟል።
አሸባሪው ቡድን ጥቃቱን የፈጸመው በሠራዊቱ ውስጥ የእኔ የሚላቸውን ሰዎች በመመልመልና በመቶ ሺህዎች የሚቆጠር ጦር በማዘጋጀት ነበር ብለዋል።
ይሁንና ቀሪው ሠራዊት በሁለት ሣምንታት መልሶ በማጥቃት የታገቱትን ማስለቀቁን፣ ወታደራዊ ክንፉ እንዲሰበርና የጁንታው አባላትም እንዲያዙ አኩሪ ገድል መፈፀሙን አንስተዋል።
ይህ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የታለመበት ቀን በየዓመቱ ታስቦ ይውላል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ዓላማው ሕዝባችንን ለቀጣይ ትግል ማነሳሳት ነው ብለዋል።
“አልረሳውም እኔም የኢትዮጵያ ሠራዊት ነኝ” የሚለው መሪ ሐሳብ የተመረጠው ኢትዮጵያን ለማዳን የተወሰዱ እርምጃዎችና የተከፈለውን መስዋእትነት ታሳቢ ለማድረግ በማለምና መላው ኢትዮጵያዊ በሁሉም መስክ የኢትዮጵያ ሠራዊት መሆን የሚያስፈልግበት ወቅት በመሆኑ ነው ሲሉ አብራርተዋል።
ዕለቱ በመጪው ጥቅምት 24/ 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት የሁሉም የመንግሥት ተቋማት ማኅበረሰብ በጋራ በመሆን ለ45 ሰከንድ እጃቸውን ከደረታቸው ላይ በማድረግ ታስቦ ይውላል።
በተጨማሪም በሻማ ማብራት፣ በደም ልገሳና በሌሎች ተግባራት ይዘከራል።
ዕለቱ የኢትዮጵያን ጠላት አንገት ለማስደፋት ቀጣይ ትግል የሚያስፈልግበት እንደሆነም አቶ ከበደ አመልክተዋል።
የሽብር ቡድኑ ጥፋት በሁሉም ኢትዮጵያዊያን የተፈጸመ ወረራ በመሆኑ ሕዝቡ ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እጅ ለእጅ ተያይዞ መታገል እንዳለበት መግለጻቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m