ደሴን ለመውረር አሰፍስፎ የነበረው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቷል።

479

ጥቅምት 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በጢጣ በኩል ሰብሮ በመግባት የደሴ ከተማን ለመቆጣጠር የሞከረው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቷል።

የመጣውን ኃይልም ደሴ ከተማ ከመግባቱ በፊት ሙሉ በሙሉ ባለበት ማስቀረት መቻሉን በወሎ ግንባር ወራሪውን ኃይል እያጸዱ የሚገኙ የመከላከያና ደኅንነት ምንጮች ጠቁመዋል።

የደሴ ከተማና አካባቢዋን ተቆጣጥረናል በማለት ጮኸው የሚያስጮሁ የወራሪው ወሬ አራጋቢዎችም በስፍራው እየተፋለመ የሚገኙትን የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ወኔና ጀግንነት ካለመረዳት የመነጨ እንደሆነ አስታውቀዋል።

በግንባሩ የተሰለፉ የሠራዊት አመራርና አባላትም ወራሪውን ኃይል ለአንዴና መጨረሻ ለማጥፋት አኩሪ ተጋድሎ እየፈጸሙ እንደሚገኝ አመላክተዋል።

በኩታበር በኩል አሰፍስፎ ደሴን ለመውረር የመጣው ወራሪ ኃይልም ምንም ማድረግ እንዳይችል ተደርጎ መደቆሱን ገልጸዋል።

በወሎ ዩኒቨርሲቲ ፎቶ ለመነሳት ገብተው የነበሩ የጥፋት ቡድኑ ፎቶ ናፋቂዎችም ባሉበት አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ እስከወዲያኛው መሸኘታቸውን ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።

ደሴና አካባቢዋን ለመውረር ከየአቅጣጫው ተሰባስቦ አሰፍስፎ የነበረውን ኃይልም አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት የደሴን ከተማ በወገን እጅ እንዳለች ማስቀጠል መቻሉን ገልጸዋል።

የደሴ ከተማ እና አካባቢው የሽብር ቡድኑን የአፈሳ ወሬ ባለመስማት አካባቢውን ጸንቶ እንዲጠብቅና ለግንባሩ ሠራዊት ሲያደርጉት የነበረውን ደጀንነት እንዲያስቀጥሉ ጠይቀዋል።

በግንባሩ ያሉ የሠራዊት አባላት የጥፋት ቡድኑን ማጽዳት ይቀጥላሉ ያሉት ምንጮቻችን በቅርብ ጊዜም ይህኑ የኢትዮጵያ ጠላት የሆነ ወራሪ ኃይልም እስከወዲያኛው የሚሸኙበት ቀን ሩቅ እንዳልሆነ አረጋግጠዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleአሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ኀይል ለመደምሰስ እድሜ እና አካላዊ ብቃቱ የፈቀደለት የአማራ ክልል ሀገር ወዳድ ዜጋ ኹሉ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 23/2014 ዓ.ም ድረስ ትጥቅ፣ ማንኛውንም መሣሪያ እና ስንቅ በመያዝ ወደ ወረዳ ማዕከል ክተቱን ተቀብሎ እንዲገባ የአማራ ክልል መንግሥት ታላቅ የኅልውና ዘመቻ አቀረበ።
Next article❝አሸባሪው የህወሓት ቡድን ሀገር ለማፍረስ በአማራና አፋር ክልል ሕዝብ ላይ እየፈጸመ ያለውን ጥፋት በጋራ በመመከት ግብዓተ መሬቱን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፈጸም በጋራ መነሳት አለብን❞ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ