
ባሕር ዳር፡ መስከረም 20/2012 ዓ/ም (አብመድ) በ17ኛው የዶሃ ዓለም አትሌቲክስ ሻምፕዮና ላይ የተካፈሉ የኢትዮጵያ የማራቶን አትሌቶች በሙሉ ለጤንነትና ለአስተዳደራዊ አሠራር ሲባል ከ3 ወር በፊት ምንም ዓይነት ውድድር ማድረግ እንደሌለባቸው በዶሃ የተገኘው የፌዴሬሽኑ አመራር ወሰነ።
አመራሩ ይህንን ውሳኔ የሚመለከታቸው ሁሉ እንዲያከብሩም በጥብቅ አሳስቧል።
ውሳኔውን መተላለፍ ከበድ ያለ እርምጃ እንደሚያስከትልም አስጠንቅቋል።
በዶሃ በተካሄደው የማራቶን ውድድር ሁሉም ኢትዮጵያን የወከሉ ሴት አትሌቶች ውድድሩን በሙቀት ምክንያት ማቋረጣቸው መገለጹ የሚታወስ ነው፡፡
ምንጭ፡- የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን