ከመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ!

1277

በሀገር መከላከያ ሠራዊት እየተመራ ወራሪውን የሽብር ቡድንና ያሰለፈውን መንጋ እየመከተ የሚገኘው መላው የፀጥታ ኀይላችን በፀረ ማጥቃት እርምጃው ቀጥሏል።

በተለይ ደሴን ለመያዝ አሰፍስፎ የመጣውን ወራሪ ኀይል በመመከት አኩሪ ገድልን እየፈፀመ ይገኛል።

ሌሊቱን ሙሉ ከተለያዩ ግንባሮች ጠጋግኖ በማሰባሰብ ደሴን ለመያዝ በኩታበር፣ ቦሩ ስላሴና በኀይቅ መስመር የመጣውን ወራሪ መንጋ የፀጥታ ኀይላችን በታላቅ ጀብዱ መክቶታል። አሁንም ደሴና አካባቢዋ በፀጥታ ኀይላችን ስር ነው።

ቀደም ብለውም ስደተኛ በመምሰልና የመከላከያ ኀይላችንን ወታደራዊ አልባሳት ለብሰው ሊዘርፉ የሞከሩ ቡድኖችና በከተማዋ የሚኖሩ ለጥፋት ኀይሉ የሚሰሩ ባንዳዎች ከትናንት ጀምሮ የጁንታውን ዓላማ ለማስፈፀም ከግንባር ውጊያው ባልተናነሰ ሲሰሩ ውለዋል።

የደሴ ወጣቶችና መላው የፀጥታ ኀላችንም ይህንን ኀይል በተደራጀ መንገድ እየመከቱት ይገኛሉ። የከተማዋ ወጣቶችም በጀመሩት መንገድ ከተማቸውን ከባንዳ የመጠበቅ ተግባራቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል።

ያለውን ኀይል ሁሉ አሰባስቦ በዚሁ ግንባር ያመጣው የሽብር ቡድኑ በጦር ግንባር ያቃተውን በወሬ ለማግኘት አሁንም መፍጨርጨሩን ቀጥሏል።
አንዳንድ የውጪ መገናኛ ብዙኀንም የሽብር ቡድኑን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ እያስተጋቡ ይገኛሉ።

በወሬ የሚያዝ ከተማ የለም ሊኖርም አይችልም ብሎ መላው ሕዝብ በደሴ ከተማ ዙሪያ ለሚነሳው አሉባልታ ጆሮ ሳይሰጥ አሁንም የሀገሩን ህልውና ለማስከበር የሚያደርገውን ተጋድሎ ቀጥሏል።

በዚሁ አጋጣሚ በተለይ ያልተጣራ መረጃን በመያዝ ሕዝብን ለማሸበር እየተንቀሳቀሱ የሚገኙና የሽብር ቡድኑ መጠቀሚያ የሆኑ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ መንግሥት ያሳስባል።

የመንግስት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየብልጽግና ፓርቲ ጥሪ።
Next articleአሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ኀይል ለመደምሰስ እድሜ እና አካላዊ ብቃቱ የፈቀደለት የአማራ ክልል ሀገር ወዳድ ዜጋ ኹሉ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 23/2014 ዓ.ም ድረስ ትጥቅ፣ ማንኛውንም መሣሪያ እና ስንቅ በመያዝ ወደ ወረዳ ማዕከል ክተቱን ተቀብሎ እንዲገባ የአማራ ክልል መንግሥት ታላቅ የኅልውና ዘመቻ አቀረበ።