የብልጽግና ፓርቲ ጥሪ።

1311

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 20/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአሸባሪው ትሕነግ ኢትዮጵያን የማፈራረስ ከንቱ ምኞትን በሚገባው ቋንቋ አስረድተን እስከወዲያኛው ላይመለስ በአጠረ ጊዜ ልንሸኘው ይገባል ሲል ብልጽግና ፓርቲ ጥሪ አቀረበ፡፡

ፓርቲው በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ባወጣው መረጃ አሸባሪው ሕወሓት ኢትዮጵያን በቅጥፈት እጆቹ ጠፍጥፎ የጋገራት ሕብስት አድርጎ በመቁጠር እሱ ባሻው ሰዓት የሚያቦካትና የሚፈረካክሳት ጡብ አድርጎ ይቆጥራታል ብሏል።

ነገር ግን ኢትዮጵያዊያንን በጎሳ እና በመንደር በመከፋፈል ኢትዮጵያ ኅልውናዋን መቼም ልታጣ አትችልም ሲል በአጽንኦት ገልጿል።

ኢትዮጵያዊነት የኅብር መገለጫ የዜግነት ክብር እና ኢትዮጵያዊ በመሆን ብቻ የሚገነዘቡት እውነት እንጂ አየር ላይ የተበተነ ጉም አይደለም ሲልም ነው ያብራራው፡፡

አያይዞም ሽብርተኛው የትሕነግ ቡድን በሀገሪቱ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ መከራ ሲዘራና ሲያሳጭድ መቆየቱን የጠቀሰው ብልጽግና ፓርቲ ነፃ አወጣዋለሁ የሚለውንም የትግራይ ሕዝብ በነፃ አውጪ ስም በርካታ ግፍና መከራ ሲያሸክመው መኖሩን አስረድቷል።

ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን አባቶቻችን ደማቸውን አፍስሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ከወራሪ ጠላት ጠብቀው ያስረከቡንን ውድ አገራችንን የወቅቱ የጋራ ጠላታችን የሆነው ትሕነግ ኢትዮጵያን የማፈራረስ ከንቱ ምኞቱን በሚገባው ቋንቋ አስረድተን እስከወዲያኛው ላይመለስ በአጠረ ጊዜ ልንሸኘው ይገባል ብሏል ፓርቲው፡፡

ኢትዮጵያዊነትን በማንኳሰስ የሚለወጥ አንዳች ነገር እንደሌለ የገለጸው ብልጽግና ፓርቲ ሀገር የሁላችንም ምሰሶ ናት ሀገር ከግለሰቦችና ከቡድኖች በላይ ናት፤ እንደ አፈ ቀላጤዎቹ ቢሆንማ ኖሮ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ልትኖር አትችልም ነበር ብሏል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleበየትኛም የኢትዮጵያ ክፍል የሚገኝ ኢትዮጵያዊ ሀገሩን ለማዳን እንዲነሳ የፌዴራል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ጥሪ አቀረበ።
Next articleከመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት የተሰጠ መግለጫ!