
ደሴ፡ ጥቅምት 19/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትህነግ ቡድን ዛሬም በሐሰት ፕሮፖጋንዳው የደሴ ከተማ ነዋሪዎችን በወሬ ለመፍታት ቢሞክርም አልተሳካለትም፡፡
በስፍራው የሚገኘው የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የጋዜጠኞች ቡድን እንደተመለከተው የደሴ ከተማ በተረጋጋ የተለመደ እንቅስቃሴዋ ቀጥላለች፡፡
በከተማዋ ሰርገው ለመግባት የሞከሩ የአሸባሪው ቡድን ተላላኪዎች መያዛቸውንና አሁንም የከተማዋ ወጣቶችና ሕዝቡ ከወገን ጦር ጋር በመሆን እየተከታተለ መሆኑን ገልጸውልናል፡፡
የከተማዋ አመራሮችም ከሕዝቡ ጋር በመሆን የተለያዩ የጸጥታ ተግባራትን እያከናወኑ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
ጀግናው መከላከያና መላው የጸጥታ ኃይል የአሸባሪ ቡድኑን አባላት በመልቀም ርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝና ቦሩ ሜዳም ሆነ ከቦሩ ሜዳ ራቅ ያሉት አካባቢዎች በጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ውስጥ መሆናቸውን የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አግልግሎት አስታውቋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m