
ባሕር ዳር፡ መስከረም 20/2012 ዓ/ም (አብመድ) የእንግሊዛዊው አትሌት ሞሐመድ ፋራህ አሰልጣኝ አልቤርቶ ሳላዛር ከአበረታች ቅመም ጋር በተያያዘ ለአራት ዓመታት ዕገዳ ተላልፎባቸዋል፡፡
ሳላዛር በ‹ናይክ› በሚደገፈው ‹ኦሪገን ፕሮጀክት› አካል በሆነ ስልጠና ከ2011-2017 (እ.አ.አ) ሞ ፋራህን አሰልጥነዋል፡፡
የአሜሪካ ፀረ አበረታች ቅመሞች ድርጅት ለአራት ዓመታት ባደረገው ምርመራና በዝግ ችሎት ለሁለት ዓመታት ባስኬደው ክስ ተሸንፈው ነው ሳላዛር እገዳው የተላለፈባቸው፡፡ አሜሪካዊው አሰልጣኙ ግን ‹‹በውሳኔው ደንግጫለሁ፤ ይግባኝም እጠይቃለሁ›› ብለዋል፡፡
‹‹የኦሪገን ፕሮጀክት በፍጹም አበረታች ቅመምን አይፈቅድም፤ ይህንን ፍትሐዊ ያልሆነ ድምዳሜ ላይ የደረሰ ውሳኔም ይግባኝ ብዬ እውነታው ላይ እንዲደረስ አደርጋለሁ›› ብለዋል የ61 ዓመቱ አሰልጣኝ፡፡
የብዙዎቹ የአልቤርቶ ሳላዛር አትሌቶች የሕክምና ባለሙያ የነበሩት ዶክተር ጀፍሬይ ብራውንም እንደ አሰልጣኙ ሁሉ ለአራት ዓመታት ታግደዋል ነው የተባለው፡፡
ምንጭ፡- ቢቢሲ