አሸባሪው ሕወሐት መሣሪያዎቹን ሲጨርስ ምላሱን መተኮስ ጀምሯል!

187

ሰሞኑን በደረሰበት ከባድ ምት ከተበታተነው ወራሪ ኃይል መካከል በጣት የሚቆጠረው በቦሩ ሜዳ አቅጣጫ በየወንዙ፣ በየጢሻውና በየሸለቆው ተደብቆ ከርሞ ነበር። ለቀናት ከተደበቀ በኋላ ርሃብና ውኃ ጥም ሲከብደው የእሩምታ ተኩስ በመክፈት ከጉድጓድ እየወጣ የአካባቢውን ሕዝብ ለማደናገር ሞክሯል። አይጥ ከጉድጓዷ በራቀች ቁጥር እንደምትመታው፣ ይሄም የተቆረጠ አሸባሪ ወዲያው ተመትቷል።

የተቆረጠው ኃይል ወደ ሲኦል እየተሸኘ ባለበት፣ በውስጥ ያሠረጓቸው ኃይሎች ጁንታው ወሎ ዩኒቨርስቲ አካባቢን እንደተቆጣጠረ በማስመል የውሸት ፕሮፓጋንዳ እየነዙ ይገኛሉ። ጀግናው መከላከያና መላው የጸጥታ ኃይላችን እነዚህን ባንዳዎች በመልቀም ርምጃ እየወሰደ ነው። ቦሩ ሜዳም ሆነ ከቦሩ ሜዳ ራቅ ያሉት አካባቢዎች በጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን እጅ ላይ ይገኛሉ።

ኅብረተሰቡ የሐሰተኛ ወሬ ፈጣሪዎችንም ሆነ አስተላላፊዎችን ለሕግ እያቀረበ አካባቢውንና ቀዬውን አሁንም በንቃት መጠበቅ ይኖርበታል።

የደሴ ከተማ ሕዝብ የሽብር ቡድኑን የሚያሸንፈው በጽናትና በትግል ብቻ ነው።

በወሬ የተገነባ ከተማ ስለሌለ፣ በወሬ የሚያዝ ከተማ አይኖርም! ሊኖርም አይችልም!

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

Previous articleጠላት ከደጅህ መጥቶ እንቅልፍ የለምና ነጻነትህን በጠንካራ ክንድህ አስከብር፡፡
Next articleየደሴ ከተማ አሁንም በተለመደ እንቅስቃሴዋ ላይ ትገኛለች፡፡