በተለያዩ የውጭ ሀገራት የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሽብርተኛው ትህነግን እየተፋለመ ላለው የመከላከያ ሠራዊት ከ150 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የዓይነት ድጋፍ አደረጉ፡፡

156

ባሕር ዳር: ጥቅምት 19/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በተለያዩ የውጭ ሀገራት የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሰሜን ምዕራብ ዕዝ ሆስፒታል በመገኘት ነው 150 ሺህ ብር የሚገመት የዓይነት ድጋፍ ያደረጉት፡፡

ከዲያስፖራው ማኅበረሰብ በተሰበሰበው ገንዘብ የተገዛውን የዓይነት ድጋፍ ያስረከቡት የኢትዮጵያ ዲያስፖራ የተግባር ምክር ቤት ሥራ አስፈጻሚ አለባቸው ደሳለኝ ዲያስፖራው ሀገርን ከብተና ለመከላከል አጥንትና ደሙን እየገበረ ለሚገኘው የፀጥታ ኃይል የሚያደረገውን ድጋፍ በቀጣይም አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት በመከላከያ ሠራዊት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ሆስፒታል ጠቅላላ አገልግሎት ኀላፊ ሌተናል ኮሎኔል ሰብለ ሙሉጌታ የሕዝብ ደጀንነት መኖሩ ሠራዊቱ የሚፈጽመውን ግዳጅ በአግባቡ እንዲወጣ ትልቅ የሞራል ስንቅ እየሆነ ነው ብለዋል፡፡

ለተደረገው ድጋፍም ምሥጋና አቅርበዋል፡፡

በቀጣይም የሽብር ቡድኑ ጨርሶ እስኪደመሰስ ድረስ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዘጋቢ፡- አዳሙ ሽባባው

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleአሸባሪው ሕወሓት የሚፈጽመውን የሽብር ተግባር ለመቀልበስ ስለሚቻልባቸው ሁኔታዎች ምክክር በማድረግ፣ በሀገር-አቀፉ የፌዴራልና የክልል መንግሥታት የሕግ አስፈፃሚዎች የግንኙነት መድረክ የተላለፈ መግለጫ !
Next articleጠላት ከደጅህ መጥቶ እንቅልፍ የለምና ነጻነትህን በጠንካራ ክንድህ አስከብር፡፡