“ጠላት በወሎ ግንባር እያደረገ ያለውን ወረራ መግታት የሚቻለው ሕዝቡ ጠላትን መውጫና መግቢያ በማሳጣት፣ እርምጃ በመውሰድና እንደ ሕዝብ ወደ አካባቢው በመትመም ነው” ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ጌታቸው ጀምበር

317

ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 18/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አማራ ታሪኩ በማሸነፍ ላይ የተመሠረተ ነው፣ ገፍቶ የሰው ክብር አይነካም፣ ክብሩን ከነኩት ግን በክንዱ ያስከብራል፣ ታሪክ ይሠራል፡፡ ጠላቶች የማይተኙለት አማራ ዛሬ ላይ በትህነግ ወራሪና ዘራፊ ቡድን በደሎች እየተፈጸሙበት ነው፤ አማራም ከኢትዮጵያዊያን ወገኖቹ ጋር በመሆን ለሕልውናው ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረገ ነው፡፡

በወቅታዊ ጉዳይ ከአሚኮ ጋር ቆይታ ያደረጉት የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ጌታቸው ጀንበር አሸባሪውና ወራሪው ቡድን አማራን በማጥፋት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ያለ የሌለ ኀይሉን ተጠቅሞ ግፍ እየፈጸመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ጠላት በወሎ ግንባር እያደረገ ያለውን ወረራ መግታት የሚቻለው ሕዝቡ ጠላትን መውጫና መግቢያ በማሳጣት፣ እርምጃ በመውሰድና እንደ ሕዝብ ወደ አካባቢው በመትመም መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በሁሉም አቅጣጫ ያለ አማራ ጠላትን መፋለም ይገባዋልም ብለዋል፡፡

በአማራ ሕዝብ ላይ በተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሰው ጥፋት መነሻው አሸባሪው ትህነግ መሆኑንም አንስተዋል፡፡ የአማራ ሕዝብ ሰላም እንዲያገኝ የትግራይን ወራሪ ኃይል መምታትና ማንበርከክ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

አሸባሪውንና ወራሪውን ቡድን አይቀጡ ቅጣት መቅጣት ካልተቻለ የአማራ ሕዝብ ሕልውና ጥያቄ ውስጥ እንደሚወደቅም ገልጸዋል፡፡

አማራ የአያቶቹንና ቅድመ አያቶቹን የጀግንነት ታሪክ ለመድገም በመስዋእትነቱ ክብሩን ማስከበር ይጠበቅበታልም ብለዋል፡፡ በዚህ የህልውና ዘመቻ ወቅት ቆሞ የሚመለከት አማራ ሊኖር እንደማይገባ ያመላከቱት ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ ሁሉም ተነስቶ ነጻነቱን ማስከበር እንደሚገባው ነው ያሳሰቡት፡፡

ከጥፋት መዳን የሚቻለው በመደራጀት፣ መስዋእትነት በመክፈልና በግንባር በመፋለም መሆኑን ነው ያመላከቱት፡፡

አማራና አፋር የተወረረው ጎረቤት በመሆናቸው ነው ያሉት ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ ሁሉም እየተናበበና እየተደራጀ ጠላትን ማጥፋት ካልቻለ ነገ ላይ መላው ኢትዮጵያ መወረሩ አይቀርም ብለዋል፡፡

በተለያዩ አካባቢዎች ጠላትን በመደምሰስ የተወረሩ አካባቢዎችን ማስለቀቅ መቻሉን ያነሱት ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ አሸናፊነት የሚመነጨው በዝግጅት መጠን መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሕዝቡ ከወገን ጦር ጋር በመሆን የጠላትን ቅስም የሚሰብር እርምጃ መውሰድ ይገባልም ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article”የአማራ ሕዝብ ነጻነቱን የሚያስከብረው በክንዱ ነው“ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ጌታቸው ጀንበር
Next articleክተት፣ ዝመት፣ መክት፣ አንክት!