በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉና ለችግር ለተዳረጉ ወገኖች 50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ እንዲደረግ ቅዱስ ሲኖዶስ ወሰነ።

212
አዲስ አበባ: ጥቅምት 18/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳይ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉና ለችግር ለተዳረጉ ወገኖች 50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ እንዲደረግ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አሳልፏል።
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ባካሄደዉ ውይይት የተለያዩ ውሳኔዎች ማሳለፉን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ተናግረዋል።
በሀገሪቱ ሰላም እንዲሰፍን ወደ እግዚአብሔር መጸለይ አስፈላጊ በመሆኑ በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የፀሎት መርኃ ግብር እንዲካሄድ ወስኗል ነው ያሉት።
በአውስትራሊያ፣ ካናዳ ፣ አውሮፓ እና በአሜሪካ ውስጥ ሆነዉ ሕዝባዊ አንድነትን ለማፈራረስ የሚጥሩ በሃይማኖት ስም የሚንቀሳቀሱ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥሪ ማቅረቡን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከዚህ በፊት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ40 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ስታደርግ መቆየቷን ያነሱት ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ አሁንም የሲኖዶሱ ምልዓተ ጉባኤ 50 ሚሊየን ብር ድጋፍ እንዲደረግ ወስኗል ብለዋል።
ዘጋቢ:- ኤልሳ ጉዑሽ -ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየአውሮፓ ሕብረት የትህነግን የሽብር ድርጊት እንዲያወግዝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጠየቁ፡፡
Next articleበወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ሕፃናት በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እየተማሩ ነው፡፡