❝ወራሪውንና ሽብርተኛውን ትህነግ ሳንቀብር ላንመለስ ተነስተናል❞ ከምዕራብ ጎጃም ዞን ከተለያዩ ወረዳዎች ወደ ግንባር ያቀኑ የፖሊስ አባላት

310

ፍኖተ ሰላም: ጥቅምት 17/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አማራን በማጥፋት ሀገር ለማፍረስ ቆርጦ የተነሳውን አሸባሪውን ትህነግን በተገኘበት ለመቅበር ሁሉም “ሆ” ብሎ ተነስቷል።

በአማራ ክልል አሸባሪው ትህነግ በወረራቸው አካባቢዎች እየፈጸመ ያለው ግፍ ያንገሸገሻቸው የምዕራብ ጎጃም ዞን የፖሊስ አባላት በእልህ እና በወኔ ወደ ግንባር ዘምተዋል።

ምክትል ሳጅን ሻለቃ አጥናፋ የባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ የቀጣና አስተባባሪ ነው አሸባሪው ትህነግ በወረራቸው አካባቢዎች ወገኖቻችንን ሲጨፈጭፍ እየሠማሁ ዝም ማለት አልችልም ብሏል።

“ጠላትን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቅበር ጊዜው አሁን ነው” ሲል ገልጿል።

ምክትል ሳጅን ሀብተማርያም አለነ ከቡሬ ከተማ የቀበሌ ማኅበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ባለሙያ ነው።

የአካባቢያችንን ሰላም ለማስጠበቅ ከኅብረተሰቡ ጋር በመሆን በርካታ የጸጥታ ሥራዎችን ስናከናውን ቆይተናል ብሏል::

አማራ ለጠላት ተንበርክኮ አያውቅም ያለው ምክትል ሳጂን ሀብተማርያም “ጠላትን ከአማራ ምድር ሳናጸዳ አንመለስም” ነው ያለው።

ኅብረተሰቡ አሁንም የአካባቢውን ሰላም በንቃት እንዲጠብቅ ዘማች የፖሊስ አባላት ጠይቀዋል።

ዞኑ ሰላሙ የተጠበቀና የተረጋጋ እንዲሆን የፖሊስ አባላት ከፍተኛ ሚና ሲጫወቱ መቆየታቸውን የተናገሩት ደግሞ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ማኅበረሰብ አቀፍ የወንጀል መከላከል ዋና ክፍል ኀላፊ ዋና ኢንስፔክተር በቀለ አብዬ ናቸው።

አሁን ላይ መንግሥት ባስተላለፈው የክተት ጥሪ መሠረት ከሁሉም ወረዳ የተውጣጡ የፖሊስ አባላት ወደ ግንባር ማቅናታቸውን ተናግረዋል።

አባላቱ ጠላትን ለመቅበር በእልህና በወኔ ተነስተዋል ብለዋል።

ክልሉ ያቀረበውን የዳግም ክተት ጥሪ ተቀብሎ በቁጭት መንፈስ ወደ ግንባር የሚዘምተው የሰው ኀይል እየጨመረ መምጣቱን የምዕራብ ጎጃም ዞን ብልጽግና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ ደጀኔ ልመንህ ገልጸዋል።

እስካሁንም የሚሊሻ አባላትና አሁን ደግሞ የፖሊስ ሠራዊት ወደ ግንባር መዝመታቸውን ተናግረዋል።

በዞኑ የአሸባሪው ትህነግ ተላላኪዎችን ትንኮሳ ለመመከት የሚያስችል የጸጥታ ኀይል በበቂ ሁኔታ መዘጋጀቱንም አስገንዝበዋል።

ማኅበረሰቡ አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅና ከዚህ ጎን ለጎን በግንባር እየተፋለመ ለሚገኘው የጸጥታ ኀይል የሚያደርገውን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

ዘጋቢ:- ዘመኑ ይርጋ – ከፍኖተ ሰላም

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleጠላት ያለበት ድረስ በነቂስ ወጥቶ መደምሰስ ለነገ የሚባል ተግባር ባለመሆኑ በአንድነት ተሰልፎ መታገል ይገባል፡፡
Next article“ጎማ በጣም ከጮኸ የመተንፈሱ ምልክት ነው!” የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት