
ደሴ: ጥቅምት 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አብዱ ሁሴን በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።
አሸባሪው ትህነግን በወሎ ምድር ቀብሮ ለማስቀረት መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖ፣ ሚሊሻና ሕዝቡ እየተፋለሙ መሆኑን ገልጸዋል።
በአሸባሪው ቡድን ላይ እየተወሰደ ባለው እርምጃ ወጣቶች በጦር ግንባር ከጠላት ጋር እየተፋለሙ እንደሚገኙም ዋና አስተዳዳሪው በመግለጫቸው አንስተዋል።
ሕዝቡም በግንባር ተገኝቶ ሠራዊቱን እየደገፈ መሆኑን ገልጸዋል።
በአሁን ወቅት በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ያሉና በውጭ ሀገርም የሚኖሩ ወገኖችም ወደ በግንባር በመሰለፍ ጠላትን በወሎ አይቀጡ ቅጣት ለመቅጣት እየታገሉ መሆናቸውንም አስረድተዋል።
አሸባሪው ትህነግ አማራን በማጥፋት ኢትዮጵያን ለማፍረስና ለውጭ ጠላቶች አጋልጦ ለመስጠት ዓላማ አድርጎ ጦርነት እንደከፈተ የገለፁት ዋና አስተዳዳሪው ይህን ወራሪ ኃይል በአንድነት መክቶ ወሎ ምድር ላይ ለመቅበር ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጋራ እንዲሳተፍ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ:- ግርማ ሙሉጌታ -ከደሴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ