
ጥቅምት 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ሀገርን አፈርሳለሁ ብሎ ከሚመጣ ማንኛውም ኃይል ለመታደግ አይደለም መዝፈን ግንባር ድረስ በመዝመት መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆኑን ድምጻዊ መስፍን በቀለ ገለጸ።
ድምጻዊ መስፍን በቀለ እንደገለጸው፤ አሁን በኢትዮጵያ የተፈጠረው ጦርነት የውስጥ ጉዳይ ብቻ ሳሆን ጠላቶች እያደረጉ ያሉት የውክልና ጦርነት ነው። ስለሆነም በፈረሰች ሀገር ላይ መነጋገር ስለማይቻል ❝ሀገሬን አፈርሳለሁ ብሎ ከሚመጣ ማንኛውም ኃይል አይደለም መዝፈን ግንባር ድረስ በመዝመት ለእናት ሀገሬ መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ ነኝ❞ ነው ያለው።
ድምጻዊ መስፍን እንደሚለው፤ በሥራ አጋጣሚ ነዋሪነቱን አሜሪካን ሀገር ቢያደርግም ከእናት ሀገር የሚበልጥ የለም ብሎ የቻለውን ኹሉ ሊሰጥ ሁርሶ የወታደሮች ማሠልጠኛ በመገኘት ሠልጣኝ ወታደሮችን በሙዚቃ እንዲበረታቱ ማድረጌ ትንሹ ተግባር ነው ብሏል።
የቀድሞው የኢትዮጵያ ሠራዊት ወታደር ልጅ ነኝ ያለው መስፍን፤ አባቱ ለእናት ሀገሩ ከ20 ዓመት በላይ በውትድርና ሙያው ሲያገለግል በካራማራ ቆስሏል፣ ደምቷል። በወታደር ሕይወት ውስጥ አለማለፌ ያስቆጨኛል የሚለው ድምጻዊ መስፍን፤ አሁን የአባቴን መስዋእትነት፣ ገድል እኔም መድገም አለብኝ ሲል መግለጹን ኢፕድ ዘግቧል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m