❝የወገን ጥምር ጦር የፀረ ማጥቃት ርምጃ፣ ወራሪውን መንጋ መውጫ መግቢያ እያሳጣው ነው❞ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት

828

ጥቅምት 15/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ጀግናው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖና ሚሊሻ በወሎ ግንባር በወረባቦ፣ በተሁለደሬ፣ ኩታበርና ደላንታ በወሰዱት የፀረ ማጥቃት ርምጃ በጠላት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እያደረሱ መሆናቸውን የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፥ ጠላት በወረባቦ፣ በተሁለደሬ፣ ኩታበርና ደላንታ አካባቢዎች ያሰለፈው ኃይል ሙትና ቁስለኛ ሆኗል።

ከጥቃቱ የተረፈውም እግሬ አውጪኝ በማለት እየፈረጠጠ ይገኛል።

ጠላት ያሰለፈው መንጋ ይዞት የመጣው መሣሪያ ገሚሱ ከጥቅም ውጭ ሲደረግ ገሚሱ ተማርኳል።

የጸጥታ ኃይሉ በወራሪው የሽብር መንጋ ላይ እያደረሰ ያለውን ከፍተኛ ኪሳራ በመሸሽ በየሸጡ፣ በየወንዙና በየጋራው እየተሽሎከሎከ የሚገኘውን የተበታተነ የጁንታ መንጋ፣ የየአካባቢው ሚሊሺያና አርሶ አደር ተደራጅቶ በመከታተል፣ የሀገር ደጀንነቱን ሊያጠናክር ይገባል።

እስካሁንም ከጀግናው የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት ጎን የቆመው የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖና ሚሊሺያ ከየአካባቢዎቹ ነዋሪ ጋር እየፈጸመው የሚገኘው አኩሪ የጦር ሜዳ ገድል ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ገልጿል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article“አሸባሪው ትህነግ በወሎ ይቀበራል” ያሉ የአዲስ አበባ ወጣቶች ወደ ወሎ ዘመቱ።
Next articleከባሕርዳር ከተማ አስተዳድር የተላለፈ የክተት ጥሪ።