“እንቅፋትና ፈተናዎቻችን አሰናክለው አያስቀሩንም፣ እንዲያውም የመሸጋገሪያ ድልድዮች ሆነው ያገለግሉናል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

177
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 15/2014 ዓ.ም (አሚኮ) እንቅፋትና ፈተናዎቻችን አሰናክለው አያስቀሩንም፣ እንዲያውም የመሸጋገሪያ ድልድዮች ሆነው ያገለግሉናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዓለማችን ላይ ቁልፍ ግኝቶች የተገኙት፣ አስደማሚ ቴክኖሎጂዎች የተሠሩትና ችግር ፈቺ መፍትሔዎች የተፈጠሩት በፈተና ጊዜ ነው ብለዋል።
በፈተና ጊዜ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ዕንቅፋትን ወደ ዕድል ለመለወጥ በሚነሡ ብርቱዎች ትጋት እንደሆነ የብዙ ሀገራት የሥልጣኔ ታሪክ ያስተምረናል።
ሁላችንም ተረባርበን ይኼንን ወቅት ለመልካም ለውጥ ከተጠቀምንበት ያለ ጥርጥር መጪው ዘመን ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና እውን የሚሆንበት ጊዜ ነው ያሉት።
በምድር በሰማይ ብለን፣ ኃይላችንን አስተባብረን፣ ክፍተታችንን ሞልተን፣ ለአንድ ዓላማ ተሰልፈን፣ በኢትዮጵያ ጠላቶች ፍጻሜ ላይ የኢትዮጵያን ብልጽግና እናበሥራለን በማለት በትዊተር ገፃቸው ገልጸዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleዓድዋ አካባቢ የሚገኘው አሸባሪው ትህነግ ወታደራዊ ትጥቅ እና ወታደራዊ አልባሳትን አመሳስሎ የሚያመርትበት ማዕከል በአየር ድብደባ ከጥቅም ውጭ ሆነ።
Next articleበኩር ጋዜጣ ጥቅምት 15/2014 ዓ.ም ዕትም