“ትግሌን የምቋጨዉ በሞት ወይም በነፃነት ነዉ” የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ተጫዋች ብርሃኑ ፈያራ

409

ደሴ፡ ጥቅምት 14/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ቡድን ተጫዋች ብርሃኑ ፈያራ አሸባሪዉን እና ወራሪዉን የትህነግ ቡድን ለመፋለም በግንባር ተገኝቷል፡፡ ብርሃኑ “ድሮ እግር ኳስ ተጨዋች ባትሆን ምን ትሆን ነበር ብለዉ ሲጠይቁኝ መልሴም ወታደር እሆን ነበር ነዉ” ይላል፡፡

ዛሬ እድሉን አገኚቶትም ብርሃኑ ወታደር ሆኗል፡፡ አሸባሪ ቡድኑ በአማራ ላይ የፈፀመዉን ወረራ ለመመከት በሚደረገዉ ትግል ተቀላቅሏል፡፡

ሕዝቡን በማደናገር ለመዝረፍ የመጣዉን ወራሪ ኀይል ሕብረተሰቡ በቅንጅት ሊታገለዉ እንደሚገባም አሳስቧል፡፡

ይህ አረመኔ ቡድን ግብዓተ መሬቱ ወሎ ላይ እንደሚፈፀም አልጠራጠርም የሚለዉ ብርሃኑ ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ ከአሉባልታ በመራቅ ትግሎን እንዲቀላቀል ጥሪ አስተላልፏል፡፡

ዘጋቢ፡- አንዋር አባቢ-ከደሴ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየደሴ ከተማ የፀጥታ ምክር ቤት ውሳኔ።
Next articleበአሉባልታ እንደማይፈቱ የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎች ተናገሩ፡፡