
የደሴ ከተማ የፀጥታ ምክር ቤት የሞተር እና ባለ3 እግር ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ እንዲቆሙ ውሳኔ አሳልፏል።
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 14/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ከዛሬ ጀምሮ የሚተገበረው ውሳኔ እስኪነሳ ወይም እስኪሻሻል ሞተር ሳይክሎች እና ባለ3 እግር ተሽከርካሪዎች በየትኛውም ሰዓት ከተማዋ ላይ መንቀሳቀስ አይችሉም።
ውሳኔው የተላለፈው የደሴ ከተማን ጸጥታና ደኅንነት ለማስጠበቅና የአሸባሪውን ትህነግ ሰርጎ ገቦች ለመቆጣጠር እንዲቻል በሚል መሆኑን የደሴ ከተማ አስተዳደር ለዋልታ ገልጿል።
ንግድ ቤቶች በተለይም መድኃኒት ቤቶች በአስቸኳይ ተከፍተው አገልግሎት መስጠት እንዲጀምሩ የፀጥታ ምክር ቤቱ ትዕዛዝ አስተላልፏል።
ውሳኔውን በማያከብሩ ላይ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስድም ምክር ቤቱ አስጠንቅቋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m