❝ሀገር ሳይከበር መኖር ስለማይቻል በአንድነት የአሸባሪውን የትህነግ ቡድን ግብዓተ መሬት ወሎ ላይ መፈጸም አለብን❞ የፋኖ አባላት

554

ደሴ: ጥቅምት 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትህነግ ቡድን በጭካኔ ንጹሐንን የጨፈጨፈው፣ ያፈናቀለው፣ የዘረፈውና ያወደመው ንብረት አልበቃ ብሎት ደሴና ኮምቦልቻ ከተሞችን ለመውረርና እኩይ ድርጊቱን ለማስቀጠል የሞት ሽረት ትግል እያደረገ ይገኛል፡፡ ይህንንም ለመቀልበስ ሁሉም እንዲዘምት ጥሪ ተላልፏል። በዚህም
አሸባሪውን የትህነግ ቡድን ለመደምሰስ የፋኖ አባላት ከአዲስ አበባ፣ ከጎንደርና ከተለያዩ አካባቢዎች በመነሳት የወገን አለኝታነታቸውን ለማስመስከር በወሎ ግንባር ተገኝተዋል፡፡

እንደ ሕዝብ የመጣውን የጠላት ኃይል በጠነከረ ትብብር ለመመከትና አይቀጡ ቅጣት ለመቅጣት የህልውና ትግል እየተደረገ ይገኛል፡፡

መኮንን ከበደ ኑሮውን በአሜሪካ ያደረገ ቢሆንም የወገን መገደልና መሰደድ ህመም ሆኖበት ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ በግንባር አብሮ መስዋእት ለመሆን የደላ ኑሮውን ትቶ ወገኑን ለመታደግ እንደመጣ ነግሮናል፡፡

በተለያዩ አካባቢዎች ጠላትን ሲፋለሙ እንደቆዩ የሚናገረው መኮንን ጠላት እንደ ሕዝብ እየተንቀሳቀሰ ዝም ብሎ የሚቆም ወጣት መኖር የለበትም፤ ተደራጅቶ መታገል አለበት ብሏል፡፡

❝ሀገር ሳይከበር መኖር ስለማይቻል በአንድነት የአሸባሪውን ቡድን ግብዓተ መሬት ወሎ ላይ መፈጸም አለብን❞ ሲል ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

ከጎንደር ተነስቶ በወሎ ግንባር የተገኘው ፋኖ ሙላቱ አድኖ (የፈራ ይመለስ) ጠላትን ለመፋለም መዝመቱን ነግሮናል፡፡ የተባበረና በአንድነት የተነሳ ኹሉ የሚያሸንፍው የለም ሲል ገልጿል።

አሸባሪውን የትህነግ ቡድን ለመደምሰስ ከሁሉም አቅጣጫ አማራ እየተመመ ነው ያለው ፋኖ ሙላቱ የቡድኑን መቀበሪያ ወሎ ላይ እናደርጋለን ብሏል፡፡

ኢንጅነር ይበልጣል ታደሰ ከአዲስ አበባ ተነስቶ የወገን አለኝታነቱን ለማሳየት በወሎ ግንባር ተገኝቷል፡፡ አሸባሪው የትህነግ ቡድን እየፈጸመ ያለው ግፍ አሳዛኝ መሆኑን ተናግሯል፡፡ ይህ ግፍ እየተፈጸመ ዝም ማለት አይቻልም ያለው ኢንጅነር ይበልጣል ጠላትን ለመደምሰስ እንደተገኘ ገልጾልናል፡፡

❝ጠላትን እስከመጨረሻው የምናጠፋበት ጊዜው አሁን ነው፤ ሁሉም ተዘጋጅቶ በአሸባሪው ትህነግ መቃብር ላይ ታሪኩን መጻፍ አለበት❞ ብሏል፡፡

ዘጋቢ:- ደጀን አምባቸው

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous article“ሽብርተኛው ትህነግን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በአንድነት ልንደመስሰው ይገባል” የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ምክትል ሊቀመንበር አቶ የሱፍ ኢብራሂም
Next article“ጎበዝ ጥይት ግዛ በወገብህ ደርድር፣ አልተደላደለም ገና ነው በጌምድር”