“ሽብርተኛው ትህነግን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በአንድነት ልንደመስሰው ይገባል” የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ምክትል ሊቀመንበር አቶ የሱፍ ኢብራሂም

336

ደሴ: ጥቅምት 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ሽብርተኛው ትህነግ ያለ የሌለ ኀይሉን ተጠቅሞ ሀገር ለማፍረስ እየተፍጨረጨረ በመሆኑ ዓላማውን ማክሸፍ እንደሚገባ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ምክትል ሊቀመንበር አቶ የሱፍ ኢብራሂም ተናግረዋል፡፡ “ሽብርተኛው ትህነግን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በአንድነት ልንደመስሰው ይገባል” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ያለምንም ልዩነት መዝመትና ወራሪውን እና ሽብርተኛው ትህነግን ድባቅ መምታት አለብን ብለዋል፡፡

አቶ የሱፍ እንዳሉት ሽብርተኛው ትህነግ የአማራና አፋር ክልሎች ላይ በፈጸመው ወረራ የዜጎች ስቃይ በርትቷል፤ ይባስ ብሎ የሽብር ቡድኑ እያደረገ ባለው ወረራ እንደ ሕዝብ ተነስቶ ደሴና ኮምቦልቻ ከተሞችን ለመቆጣጠር ያለ የሌለ ኀይሉን እየተጠቀመ ነው፡፡

ሽብርተኛው ትህነግ እያካሄደ ያለውን ወረራ ለመመከት የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኀይል፣ ሚሊሻና ፋኖ ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረጉ እንደሆነም አቶ የሱፍ ገልጸዋል፡፡

አቶ የሱፍ በዚህ ወቅት በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ትግላችንን ወደ ዳር ለመጎተት የተሰለፉ ኀይሎች ከድርጊታቸው መቆጠብ አለባቸው ሲሉ አሳስበዋል፡፡

ሽብርተኛው ትህነግን መመከትና ማጥፋት የታሪክ፣ የክብር እና የማንነት ጉዳይ ነው ያሉት አቶ የሱፍ ሕዝቡን በሐሰት በፕሮፖጋንዳ ለመፍታት እየጠቀመበት ያለው መንገድ ያረጀ ያፈጀ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የተወለድንበት እና ያደግንበትን ምድር ለቀን የትም መሄድ የለብንም ያሉት አቶ የሱፍ ሁሉም በአንድነት በመነሳት አሸባሪውን ቡድን ቀመደምሰስ ታሪክ የሚሠራበት ጊዜው አሁን ነው ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ደጀን አምባቸው -ከደሴ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleየሐሰት ፕሮፖጋንዳ – የሽብርተኛው ትህነግ የተለመደ እና ጊዜ ያለፈበት የጦርነት ስልት
Next article❝ሀገር ሳይከበር መኖር ስለማይቻል በአንድነት የአሸባሪውን የትህነግ ቡድን ግብዓተ መሬት ወሎ ላይ መፈጸም አለብን❞ የፋኖ አባላት