
ጥቅምት 13/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ሽብርተኛው ትህነግ ከጥንስሱ በተለያዩ የብዙኃን መገናኛ እና ለዚህ ዓላማ በተቋቋሙ ቡድኖች አማካይነት በሚያሰራጨው የበሬ ወለደ ወሬ ሕዝብን ያደናግር እንደነበር ይታወቃል። ይህ ባህሪው በሥልጣን ላይ በነበረበት ወቅትም ጭምር ምናባዊ ድርሰት በመጻፍ ሲቆጣጠራቸው በነበሩ ልሳኖቹ የተለመደውን የሐሰት ፕሮፓጋንዳ በማሰራጨት ሕዝብን ሲያደናግር፣ የማኅበረሰቡን እውነተኛ ታሪክ እና እሴት ሲሸረሽር ቆይቷል።
ከመንበረ ስልጣኑ ከተባረረ በኋላም በልሳኖቹ እና በህቡዕ ባደራጀው ማኅበራዊ ሚዲያ ቡድን የሐሰት ፕሮፓጋንዳውን በመንዛት የተለመደውን ሕዝብን የማደናገር ሥራ እየሠራ ይገኛል፡፡
የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ኀላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ አሸባሪው ትህነግ የሐሰት ፕሮፓጋንዳ ሲጋት ያደገበት የተለመደ እና ጊዜ ያለፈበት ማደናገሪያ ሥልቱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በተለይ ደግሞ ያልተያዘውን ቦታ እንደተያዘ በማስመሰል ማኅበረሰቡን ማደናገር የተለመደ ሴራው መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ለሀገሪቱ አንድነት የሚያስብ ማንኛውም አካል የሽብርተኛው ትህነግን የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ተከታትሎ ማክሸፍ እና በተቀናጀ መንገድ መፋለም እንደሚገባም አቶ ግዛቸው አሳስበዋል፡፡
የሚሰራጩ መረጃዎችንም ከታማኝ የብዙኃን መገናኛ ተቋማት ማረጋገጥ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ ማኅበራዊ አንቂዎችም ሀገር አፍራሽ የኾኑ ዘገባዎችን ከመልቀቅ እንዲቆጠቡ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ለሽብርተኛው ትህነግ ወራሪ ቡድን የሐሰት ወሬ ጆሮ ባለመስጠት ሁሉም የህልውና ዘመቻውን መቀላቀል እና ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባው አቶ ግዛቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሠራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m