
ባሕር ዳር፡ መስከረም 20/2012 ዓ/ም (አብመድ) የሩስያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክስርቲያን የውጪ ጉዳይ ኃላፊዎችና የሩሲያ የሚዲያ አባላትን ያካተተ ልዑክ ጎንደርን እና በውስጧ የሚገኙ ቅርሶችን እየጎበኙ ነው።
ዘጠኝ አባላት ያሉት የልዑክ ቡድኑ አባላት ዛሬ ረፋድ ላይ ደብረ ብርሃን ሥላሴን እና የዓፄ ፋሲል አብያተ-መንግሥትን ጎብኝተዋል።
ለሁለት ቀናት በጎንደር ከተማ በሚኖራቸው ቆይታም የአብነት ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ በኢትዮጵያ ብቸኛ የሆነውን የባታ ደብረ ኃይል ወደብረ ጥበብ ባሕታ ለማሪያም ካቴድራል የአቋቋም ትምህርት ቤትን ይጎበኛሉ፡፡
በጎንደር ከተማ የሚገኙ የመንበረ መድኃኒዓለም እና የቁስቋም ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናትን እንደሚጎበኙ ታውቋል።
ዘጋቢ፦ ፍፁምያለምብርሃን ገብሩ