
የአሸባሪው የህወሓት ቡድን ማሰልጠኛ ማዕከል ዛሬ የአየር ጥቃት ዒላማ ሆነ።
ጥቅምት 12/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአሸባሪው የህወሓት ቡድን ማሰልጠኛ ማዕከል ዛሬ የአየር ጥቃት ዒላማ መሆኑን የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ አስታውቋል።
ማዕከሉ ለአሸባሪው ቡድን ወታደራዊ ሥልጠና ከመዋሉ በፊት የኢፌዴሪ መከላከያ ማሠልጠኛ ማዕከል እንደነበርም ተገልጿል።
በአሁኑ ወቅት አሸባሪው ቡድን በዚህ ተቋም ውስጥ ወታደራዊ ስልጠና የሚሠጥበት፤ የውጊያ ግንኙነት ኔትወርክ ያለበት መሆኑን የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ አመላክቷል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m