❝ጠላትን እቶን እሳት ሆነን በመለብለብ እውነተኛ የአባቶቻችን ልጆች መሆናችንን ማሳየትና ማረጋገጥ ይጠበቅብናል❞ የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር

252
ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር በወቅታዊ ጉዳይ መልዕክት አስተላልፏል።
ዞኑ ያስተላለፈው መልዕክት ቀጥሎ ቀርቧል:-
የደቡብ ወሎ/የአማራ ወጣት ሆይ!
ታሪካዊ ጠላትህ ትህነግ አንተን፣ ቤተሰብህን፣ ወዳጅና ወገንህን እየገደለ፣ ጥረህ ግረህ ያፈራኸውን ሐብትና ንብረትህን እየዘረፈ፣ በየአካባቢው የምትገለገልባቸውን የግልና የመንግሥት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት እያወደመ በእርግጥም እውነተኛ ጠላትነቱን በተግባር እያሳየህ ነው።
ጠላት ከዚህ በላይ ውድመት እንዳያስከትል እኛ ጠላትን እቶን እሳት ሆነን በመለብለብ እውነተኛም የአባቶቻችን ልጆች መሆናችንን ማሳየትና ማረጋገጥ ይጠበቅብናል።
ስለሆነም ጠላት የሚያደርስብን የግፍና መከራ አመድ መተንተን አቁመን ጠላት የእኛን ጀግንነትና ፋኖነት እንዲተነትን ማድረግ የምንችለው እኛ የተቆጣንና የጠላትን ግፍ የማንሸከም ሕዝብ መሆን ስንችልና ፍም እሳቱን መጨበጥና መትፋት ስንችል ብቻ ነው።
ይህን ነቀርሳ የሆነ ጠላት ለመመከትና ለማጥፋት ዋናውና ትልቁ አቅማችን የእኛ በትብብርና በአንድነት ሆ ብሎ በአንድነት በመዝመት ጠላትን መግቢያና መውጫ ማሳጣት ብቻ ነው።
ስለሆነም፦
1. ሁሉም መዝመት የሚችል አካል በቀጥታ ከመለዮ ለባሹ ጋር በጋራ በግንባር ተሰልፎ አማራዊ ጀግንነቱን ያሳይ፣ ታሪካዊ ኃላፊነቱንም ይወጣ! ያለ እኛ ክቡር መስዋእትነት ነጻነትና ክብር አይገኝምና የደቡብ ወሎ ወጣት፣ ደሴ ከተማ ላይ የከተመ የሰሜን ወሎ ወጣት/መላው አማራ አሁንም ክተትና ክንድህን በጠላት ላይ እንድታነሳ ዳግም ጥሪ ቀርቦልሃል።
2. ሕዝባችን ለሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ለአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ የሚያደርገውን የስንቅ፣ የውኃና ሌሎች ለጦርነቱ አጋዥ የሆኑ የሎጀስቲክ ድጋፎችን አጠናክሮ በመቀጠል ለህልውናው ይዋደቅ ዘንድ ጥሪ እናቀርባለን።
3. ኀብረተሰቡ እንቅስቃሴያቸው አጠራጣሪ የሆኑ ጸጉረ ልውጥ ግለሰቦችን በአካባቢው ለሚገኙ የጸጥታ አካላት እየያዘ በማስረከብ የሠርጎ ገቦችን እንቅስቃሴ በማምከን ለጦርነቱ ያለውን ደጀንነት በተግባር እንዲያረጋግጥ የከበረ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ግፍን አንለማመድ፤ ጠላታችንን ለይተን እንወቅ፣ ከሀገር መከላከያ ሠራዊትና ሌሎች በህልውና ትግሉ ከተሰለፉ የጸጥታ ኃይሎቻችን ጎን እንቁም!
ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም
የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article❝ሕዝቡ አሸባሪውን የትህነግ ኃይል በመቅበር ራሱን ከሰቆቃ ሀገሩን ከዓለም አቀፍ ጫና መታደግ አለበት❞ የአብን የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ
Next articleከመከላከያ ሕዝብ ግንኙነት የተሰጠ መግለጫ ።