❝ሕዝቡ አሸባሪውን የትህነግ ኃይል በመቅበር ራሱን ከሰቆቃ ሀገሩን ከዓለም አቀፍ ጫና መታደግ አለበት❞ የአብን የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ

258
ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ሕዝቡ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በአንድነት ተነስቶ አሸባሪውን ትህነግ በማስወገድ ራሱን ከሰቆቃ ሀገሩን ከዓለም አቀፍ ጫና መታደግ አለበት ሲሉ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ ገለጹ፡፡
አቶ ክርስቲያን እንደገለጹት አሸባሪው ትህነግ በሰሜን እዝ ላይ አሰቃቂና አስነዋሪ ጥቃት ከፈጸመ ወዲህ በተለያዩ ጊዜያት በአማራና አፋር ክልሎች ንጹሐን ዜጎችን ዒላማ ያደረገ ጅምላ ጭፍጨፋዎችን ፈጽሟል፡፡
ወራሪ ቡድኑ አሁንም ሀገር ለማፍረስ ያለ የሌለውን አቅሙ ተጠቅሞ በከፍተኛ ሁኔታ እየተፍጨረጨረ ይገኛል፡፡ ሕዝቡ አሸባሪውን ትህነግ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በመቅበር ራሱን ከሰቆቃ ሀገሩን ከዓለም አቀፍ ጫና መታደግ አለበት ብለዋል፡፡
አሸባሪው ትህነግ ንጹሐን ዜጎችን እየጨፈጨፈ ቢሆንም በቅጥረኞቹ አማካኝነት በዓለም መድረክ ተበዳይ በመምሰል ኢትዮጵያ ላይ የውጭ ጫና እንዲደረግባት እየሠራ መሆኑን ያነሱት አቶ ክርስቲያን፣ ሕዝቡ በአንድነት ተነስቶ ቡድኑንና እኩይ ድርጊቱን ካላስወገደ ሰቆቃው እንደሚቀጥልና በኢትዮጵያ ላይ የሚደረጉ ጫናዎችም እየበረቱ እንደሚሄዱ ገልጸዋል፡፡
የሽብር ቡድኑ በሀገሪቱ ላይ የፈጸማቸው በደሎችና ሴራዎች በሀገሪቱ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን በምዕራባውያንና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጭምር ይታወቃል ያሉት አቶ ክርስቲያን፤ በአሁኑ ጊዜም ወራሪው ቡድን በአማራና በአፋር ክልሎች ነፍሰጡር ሴቶችን፣ አቅመ ደካሞችና ሕጻናትን በጭካኔ የጨፈጨፈ ቢሆንም የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በዝምታ ማለፉ የሚያሳዝንና የሚያስተዛዝብ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ በአንጻሩ ምዕራባውያን የንጹሐን ዜጎች ህይወት ለመታደግ የሚደረግ እንቅስቃሴን በማውገዝ ማዕቀብ ለመጣል መሸቀዳደማቸው የሚኮነን ተግባር መሆኑን መግለጻቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article❝ሁሉም ወደ ወሎ ይትመም፣ ይዝመት❞ ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ
Next article❝ጠላትን እቶን እሳት ሆነን በመለብለብ እውነተኛ የአባቶቻችን ልጆች መሆናችንን ማሳየትና ማረጋገጥ ይጠበቅብናል❞ የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር