በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአሸባሪው ትህነግ ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ190 ሺህ ዶላር በላይ ድጋፍ አደረጉ።

144
ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአሜሪካን ሀገር ዴንቨር፤ አውሮራና አካባቢው ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያን በሽብርተኛው ትህነግ የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመርዳት ከ190 ሺህ በላይ ዶላር ድጋፍ ማድረጋቸው ተገለጸ።
ዴንቨር፣ አውሮራና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከቤይ ኤርያ ቀጥሎ ሁለተኛውን ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጋቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ፍጹም አረጋ አስታውቀዋል።
አምባሳደሩ እንደገለጹት ኢትዮጵያውያኑ በሽብርተኛው ትህነግ በግፍ የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመርዳት ከ190 ሺህ ዶላር በላይ ድጋፍ አድርገዋል።
በአሜሪካ ከወገን ለወገን የሚደረገው ድጋፍ እየጨመረ መሆኑንና በሌሎች ቦታዎችም ድጋፍ ለማካሄድ ዝግጅት በመደረግ ላይ እንደሚገኝም አምባሳደሩ ገልጸዋል።
ዝግጅቱ እንዲሳካ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት፣ ለአርቲስት ተስፋዬ ሲማ እና ለለጋሾች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleደሴና አካባቢዋ በተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ።
Next articleአሸባሪው የትህነግ ኃይል በዛሪማ ከተማ በሚገኘው መስጂድ ላይ የፈጸመውን ውድመት የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አወገዘ።