
ጥቅምት 11/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ትናንት ማምሻውን ሐይቅ ከተማ በጠላት እጅ እንደወደቀች ተደርጎ በአንዳንድ የጠላትን አጀንዳ በሚያራግቡ ቅጥረኛ ኃይሎች ሲቀርብ የነበረው የበሬ ወለደ አሉባልታ ሐሰት ነው።
ሐይቅ ከተማ አሁንም በሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ቁጥጥር ሥር ስትሆን የዞን፣ የተሁለደሬ ወረዳና የሐይቅ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ከጸጥታ ኃይሉ ጋር ተቀናጅተው አመራር በመስጠት ላይ ይገኛሉ።
አሸባሪው፣ ጨፍጫፊው፣ ዘራፊውና ወራሪው የትህነግ ኃይል በውጫሌ፣ ተሁለደሬ፣ ወረባቦና ደላንታ ግንባሮች ጦርነት የከፈተ ቢሆንም ሕዝቡ ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመቀናጀት ሰርጎ ለመግባት እየሞከረ ያለውን ወራሪ ኃይል ወደ ቀሪ አካባቢዎች እንዳይገባ በአንድነት በመዝመት መመከት እንዲሁም አካባቢውን ከጸጉረ ልውጥ በመጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ የደቡብ ወሎ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት አቅርቧል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m