በቻይና ቤጂንግ ወታደራዊ ትርዒት እየቀረበ ነው፡፡

248

ባሕር ዳር፡ መስከረም 20/2012 ዓ/ም (አብመድ) ቻይና በኮሙኒስት ፓርቲ መመራት የጀመረችበትን 70ኛ ዓመት እያከበረች ነው፤ የበዓሉ ድምቀት አካል የሆነ ወታደራዊ ትርዒትም በቤጂንግ እየተካሄደ ነው፡፡

ቻይና በኮሙኒስት ፓርቲ መመራት የጀመረችው በ1942ዓ.ም በዛሬው ቀን ነው፤ በወቅቱ የፓርቲው መሪ ማዖ በቲያንሚን አደባባይ ቆመው ‹ሕዝባዊት ሪፐብሊክ ቻይና› መመሥረቷን የተናገሩት በዚሁ ቀን ከ70 ዓመታት በፊት ነው፡፡

በወቅቱ በተካሄደ ወታደራዊ ሰልፍም 17 የጦር ጀቶች በቤጂንግ ሰማይ ላይ ወታደራዊ ትርዒት በማሳዬት ሁነቱን አድምቀው ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ በልዩ ልዩ ወታደራዊ ትርዒቶች እቀረቡ ነው፡፡

የኮሙኒስት ፓርቲው ቻይናን ባለፉት 70 ዓመታት በማኅበራዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊና መሠረተ ልማት ዘርፎች ብዙ ርቀት ማራመዱ ይነገራል፡፡ አሜሪካን መገዳደር የሚችል ምጣኔ ሀብት መገንባትም ችሏል፡፡ በአንጻሩ ምዕራባውያኑ የዴሞክረሲ ፀር እንደሆነ በመግለጽ ፓርቲውን ይተቹታል፤ ቻይናውያን ግን ለ70ኛ ጊዜ የፓርቲን የሀገር ምሥረታ በዓል በድምቀት እያከበሩ ነው፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

Previous articleበአማራ ክልል ባለፈው በጀት ዓመት መጠናቀቅ የነበረባቸው 17 ድልድዮች ወደ 2012 በጀት ዓመት ተላልፈዋል ተባለ፡፡
Next article28ኛው ሀገር አቀፍ የአረጋውያን ቀን በሚሊኒዬም አዳራሽ እየተከበረ ነው፡፡