❝ከበባዎች ኹሉ ይቀለበሳሉ፤ ኢትዮጵያም ታሸንፋለች❞ ብልጽግና ፓርቲ

511
ጥቅምት 10/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ብልጽግና ፓርቲ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ባስተላለፈው መልዕክት አሸባሪው ቡድን ከተበተነበት ተሰብስቦ ለሀገር ህልውና ስጋት እንዲሆን እጃቸውን የዘረጉለት፣ የመገናኛ ዘዴዎችን ያቀረቡለት፣የእርዳታ እህል እየበላ ኢትዮጵያን እንዲወጋ ያደረጉት የኢትዮጵያ ጠላቶች መኖሯን የማይሹ፣ ከማንቀላፋት መንቃቷ ያስፈራቸው ታሪካዊ ጠላቶቿ ናቸው ብሏል።
ዛሬ በሕዝቡ ላይ ለሚደርሰው የበቀል መከራ ትላንት በሰብዓዊነት ስም የተደረጉ እንቅስቃሴዎች የአንበሳውን ድርሻ ይይዛሉ ያለው ፓርቲው በዚህ ብቻ ሳያበቃም ኢትዮጵያ ደምታ ከምትጮኸው ድምፅ በላይ አሸባሪው ቡድን የሚያሰማውን የተኩላ ድምፅ ኾነ ተብሎ ጆሮ በመስጠት ጥብቅናቸውን በተለያየ ጊዜ ሲያሳዩ ታይተዋል ሲል ገልጿል።
ይህም አካሄድ በርካቶች ከኢትዮጵያ ጋር የነበራቸውን ታሪካዊ ግንኙነት ከግምት ውስጥ ያላስገባ፣ የአሸባሪ ቡድኑን ትክክለኛ ማንነት የዘነጋ ኾኗል፤ በተደጋጋሚ ይህን አካሄድ በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ለመቀልበስ የተለያዩ ሙከራዎች ቢደረጉም አሸባሪው ቡድኑን ዳግም ለማንገሥ የሚፈልጉ ኃይሎች ኢትዮጵያ ላይ ካላቸው የጠነከረ ኢኮኖሚያዊ፣ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ፍላጎቶች አንፃር እምብዛም ፍሬ ሳያፈራ ቀርቷል ብሏል።
❝የኢትዮጵያን ሀቅ ተረድቶ በጦርነት ከፍተኛ መከራ ውስጥ የገባውን ሕዝባችንን ከመርዳት ይልቅ ዛሬም ድረስ የቀጠለውን የደቦ ከበባ ለመቀልበስ ከሕዝባችን ጋር ኾነን ለመቀልበስ ያላሰለሰ ጥረት እያደረግን እንገኛለን❞ ነው ያለው ፓርቲው።
መላው ሕዝብም ይህንን ኢትዮጵያ ላይ እየተቃጣ የሚገኘውን የህልውና ስጋት ለመመከት ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነቱን በማጠናከር፣ ትንኮሳዎችን በማክሸፍ ዳግም የሀገር አለኝታነቱን ሊያስመሰክር እንደሚገባው ብልጽግና ፓርቲ ገልጿል።
❝ከበባዎች ኹሉ ይቀለበሳሉ፤ ኢትዮጵያም ታሸንፋለች❞ ብሏል ፓርቲው ባስተላለፈው መልዕክት።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article❝የመከላከያ ሠራዊት ጥቃቶቹ ዒላማ ያደረጉት የህወሓት የጦር መሣሪያ ማምረቻ ፤ማከማቻ እና የጦር ትጥቅ ጥገና ጣቢያዎችን ብቻ ነው❞ የኢትዮጵያ ወቅታዊ መረጃ ማጣሪያ
Next articleአሸባሪው ትህነግ በሰሜን ጎንደር ዞን አዳርቃይ ወረዳ ዛሪማ ከተማ የሚገኘውን መስጂድ ማውደሙን የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ገለጸ፡፡