❝ወሎ ለፍቅር እንጅ ለጠላት አይንበረከክም❞ የደሴና አካባቢው ነዋሪዎች

292
ደሴ፡ ጥቅምት 10/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በደሴና አካባቢው የሚኖሩ ሴቶች ማኅበረሰቡ ለህልውና ትግሉ እንዲነሳ ትዕይንተ ሕዝብ እያካሄዱ ነው።
ሕዝቡ ለህልውናው ዘመቻ ከፊት ቀድሞ እንዲሰለፍም ባካሄዱት ትዕይንተ ሕዝብ ጠይቀዋል፡፡ ከፊት ተሰልፈው ጠላትን ለመደምሰስ ዝግጁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።
❝ሀገራችንን ተዳፍሮ በሕዝባችን ላይ ግፍ እየፈጸመ ያለውን አሸባሪውና ወራሪው የትህነግ ኃይል በአንድነት ቁመን እንመክታለን❞ ብለዋል ባካሄዱት ትዕይንተ ሕዝብ፡፡
ሴቶች ከወንዶች እኩል ቁመን አሸባሪውን እና ወራሪውን ትህነግ ኃይል ግብዓተ መሬት እንፈፅማለን በሚል ወጣቶችን እያበረታቱና ለህልውናው ዘመቻው ድጋፍ እያደረጉ ይገኛሉ።
በከተማው በመዘዋወርም ❝ወሎ ለፍቅር እንጅ ለጠላት አይንበረከክም፣ ለህልውናችን እንሞታለን፣ታጠቅ፣ ዝመት፣መክት፣ አንክት፣እኛ የጣይቱ ልጆች ነን፣ለሀገራችን የማንከፍለው መስዋእትነት የለም❞ የሚሉ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ፡-ግርማ ሙሉጌታ-ከደሴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየሽብርተኛው ትህነግን ፍፃሜ ለማፋጠን የፀጥታ ኀይሉ የሚሰጣቸውን ግዳጅ በብቃት እየተወጡ መሆኑን የመቄት ወረዳ ሕዝባዊ ሠራዊት አባላት ተናገሩ፡፡
Next article❝የመከላከያ ሠራዊት ጥቃቶቹ ዒላማ ያደረጉት የህወሓት የጦር መሣሪያ ማምረቻ ፤ማከማቻ እና የጦር ትጥቅ ጥገና ጣቢያዎችን ብቻ ነው❞ የኢትዮጵያ ወቅታዊ መረጃ ማጣሪያ