በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ፣ በእስራኤል እና በአሜሪካ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችና ወዳጆች በሽብርተኛው ትህነግ ወረራ ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረጉ፡፡

152
ደባርቅ: ጥቅምት 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ፣ በእስራኤል እና በአሜሪካ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችና ወዳጆች በሽብርተኛው ትህነግ ወረራ ተፈናቅለው በደባርቅ ከተማ ለተጠለሉ ወገኖች ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የምግብ እና አልባሳት ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ድጋፉን ካስረከቡት ተወካዮች መካከል አቶ ደረጀ ሽፈራው ለወገን ደራሽ ወገን ነው በሚል በአሜሪካ፣ በእስራኤል እና በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ከሚኖሩ አማራዎችና ወዳጆች በሰበሰቡት ገንዘብ የተገዛውን ምግብና አልባሳት ወደ ደባርቅ ማምጣታቸውን ገልጸዋል፡፡
ከተፈናቃይ ወገኖች ብዛትና ከችግሩ አሳሳቢነት አንፃር የተደረገው ድጋፍ በቂ አለመሆኑን ተናግረው ወደፊትም የተጠናከረ ድጋፍ ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡
ሌላኛው ተወካይ አቶ ጥጋብ አንበርብር አሸባሪው ትህነግ እንዲደመሰስና የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ አካባቢያቸው እንዲመለሱ ኹሉም ሊረባረብ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
ድጋፉን የተረከበው የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽሕፈት ቤት በዞኑ ያለውን ችግር በመረዳት ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምሥጋና አቅርቧል፡፡
ዘጋቢ፡- አድኖ ማርቆስ-ከደባርቅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበወልድያ እና ትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተወሰነ።
Next articleበአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ማቋቋሚያና ሥልጣንና ተግባራቱን መወሰኛ አዋጅ