በወልድያ እና ትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎች በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተወሰነ።

136
ጥቅምት 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአሸባሪው የትህነግ ቡድን በተፈጠረው ችግር ምክንያት በወልድያና ትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች በጊዜያዊነት ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
በወልድያና ትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች በጊዜያዊነት ለመመደብ የመመዝገቢያ ገጽ ተከፍቶ ተማሪዎች እንደሚመዘገቡ እና ምደባ እንደሚካሄድም ተገልጿል፡፡
በዚህም በዩኒቨርስቲዎቹ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች አስፈላጊውን የትምህርት ማስረጃቸውን በማዘጋጀት ከጥቅምት 09/2014 ዓ.ም ጀምሮ መመዝገብ እንደሚችሉ ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleአሸባሪው ትህነግ የጀመረውን ጦርነት ለመመከት ሁሉም ኅብረተሰብ ከጸጥታ አካላት ጎን እንዲሰለፍ መንግስት ጥሪ አቀረበ።
Next articleበአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ፣ በእስራኤል እና በአሜሪካ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችና ወዳጆች በሽብርተኛው ትህነግ ወረራ ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረጉ፡፡