
ባሕር ዳር፡ መስከረም 20/2012 ዓ/ም (አብመድ) ‹አምነስቲ ኢንተርናሽናል› የተሰኘው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እንዳስታወቀው በመጋቢት ወር በሶማሊያ በተፈፀመ የአየር ጥቃት ንጹኃን አርሶ አደሮች መገደላቸውን በምርመራ አረጋግጧል፡፡ በወቅቱ የተገደሉት ሦስት አርሶ አደሮች ከቀጠናው አሸባሪ አልሸባብ ጋር ግንኙነት እንደነበራቸው አሜሪካ ማስረዳት አለመቻሏንም በምርመራ ማረጋገጡን ነው የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ያስታወቀው፡፡
አርሶ አደሮቹ ከእርሻ ቦታ ወደ ቤታቸው በመኪና በመመለስ ላይ እያሉ ነበር በአሜሪካ የአፍሪካ እዝ ጥቃት የተፈጸመባቸው፡፡
በአምነስቲ ኢንተርናሽናል የሶማሊያ ሁኔታ ተመራማሪ አብዱላሂ ሐሰን ‹‹የአሜሪካ የአፍሪካ እዝ በዒላማውና በአየር ጥቃቱ የሚመጣውን ውጤት የማያውቅ፤ ንጹኃንን የሚያጠቃ ነው›› ብለዋል፡፡
በመጋቢት ወር የአሜሪካ የአፍሪካ እዝ አጣራሁ ባለው መረጃ መሠረት የሞቱት ቱሪስቶች እንደሆኑ ገልጾ ነበር፤ ይህም ግን መልሶ ንጹኃንን ለመግደሉ ማስረጃ ከመሆን አላለፈም፡፡ ሟቾች ቱሪስትም ሆኑ አርሶ አደር የጥቃቱ ዒላማ መሆን ያልነበረባቸው ናቸውና፡፡
ምንጭ፡- ቢቢሲ