የመውሊድ በዓልን ከተቸገሩ ወገኖች ጋር በጋራ ማክበር እንደሚገባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አሳሰበ፡፡

277

አዲስ አበባ፡ ጥቅምት 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ የፊታችን ሰኞ የሚከበረውን 1496ኛውን የነቢዩ መሐመድ የመውሊድ በዓልን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም በነቢዩ መሐመድ መውለድ ብዙ መልካም ነገሮች አግኝተናል፤ እሳቸው ስለሰውልጅ የተፈጠሩ ነብይ ናቸው፤ መውሊድ የተንኮል ሥራ የተቀበረበት፣ ሰይጣን የተዋረደበት፣ የሰው ልጅ በመልካም ነገሮች እንዲሞላ የተደረገበት ነው ብለዋል።

የሰውን ልጅ ወደ ጀነት የመራ ነው፤ መወለዳቸው ለእኛ ፀጋ ሆኖናልም ብለዋል።

በዓሉ ሲከበር የነቢዩ መሐመድ በረከቶችን በማሰብና መንገዳቸውን በማክበር እንዲሆንም አሳስበዋል።

የተቸገሩ ወገኖች ጋር በዓሉን በጋራ ማክበር እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ መንግሥት በሀገራችን እያየን ያለነው የሰው ልጅ ግድያና መፈናቀል እንዲቆም ማድረግ አለበትም ነው ያሉት።

በአሁኑ ወቅት ሕዝበ ሙስሊሙ ለተቸገሩ ወገኖች ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም ገልጸዋል። የማከፋፈል ሥራውን የሚሠሩ ተቋማት በተገቢ መልኩ ለተጎጂዎች እንዲደርስ ማድረግ አለባቸውም ብለዋል። በዓሉ ሀገር ሰላም የምትሆንበትና የሚያፈቃቅር እንዲሆንም ተመኝተዋል።

ዘጋቢ፡- ዘመኑ ታደለ -ከአዲስ አበባ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleአፍሪካውያን ዘላቂ ሰላማቸውን ለማስጠበቅ በራሳቸው የገንዘብ አቅም የሚደገፍ ተቋምን ለማጠናከር 480 ሚሊየን ዶላር ከአባል ሀገራቱ እያሰባሰበ መሆኑን የአፍሪካ ሕብረት ገለጸ፡፡
Next article“የፖለቲካ መሪዎች ቅንነትን ተላብሰው በዜጎች ላይ የሚደርሰውን ሞትና መፈናቀል ማስቆም አለባቸው” የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር