
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 04/2014 ዓ.ም (አሚኮ)ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ዛሬ በቤጂንግ በተጀመረው 2ኛው የተመድ ዓለም አቀፍ ዘላቂ የትራንስፖርት ኮንፈረንስ መክፈቻ ላይ በመገኘት ንግግር አድርገዋል። በዚህ ወቅትም የመንገድ መሠረተ ልማት በግብርና ላይ ለተመሰረተው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት እና ዋነኛ የልማት አጀንዳ በመሆኑ ከዓመታዊ በጀቷ 11 በመቶ ለመንገድ መሠረተ ልማት እና ጥገና መድባለች ብለዋል።
ኮንፍረንሱ እንደ ኢትዮጵያ ወደብ አልባ ለሆኑ ሀገሮች ትኩረት እንደሚሰጥ ተስፋቸውን ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንቷ በአነስተኛ የገጠር ከተሞችም ሆነ በአዲስ አበባ የሰዎችንና የቁሳቁስ ዝውውርን ለማፋጠን በቀላል የኤሌክትሪክ ባቡርም እና ፈጣን የመጓጓዣ ሥርዓት በመፍጠር ጉዞን አስተማማኝ ማድረግ ለዘላቂ ልማት መምጣት ወሳኝ መሆኑን አጽኖት ሰጥተው እንደተናገሩ ከፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m