በሀገር ውስጥ የተፈጠሩ ችግሮችን በኢትዮጵያ መር በአፍሪካ ድጋፍ ለመፍታት እየተሠራ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ።

213
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 04/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ይህን ያሉት ዛሬ በተጀመረው በ39ኛው የአፍሪካ ህብረት መደበኛው የአስፈፃሚ ምክርቤት ስብሰባ ላይ ነው።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በይፋ ስለተጀመረው የአፍሪካ ህብረት የአስፈፃሚ ምክርቤት ስብሰባን አስመልክተው ለመገናኛ ብዙኃን ማብራሪያ ሰጥተዋል።
አምባሳደር ዲና እስከ ነገ በሚቆየው ስብሰባ የኮሮና ቫይረስ ተፅዕኖ፣ የክትባት ተደራሽነት እና የምርምር ሥራዎች እንዲሁም የአፍሪካ ሕብረትን ማጠናከር ላይ ትኩረት ያደረጉ ጉዳዮች እንደሚቀርቡ ገልጸዋል።
ቃል-አቀባዩ እንዳሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ እና ያጋጠሟትን ችግሮች በራሷ ለመፍታት እያደረገች ያለውን ጥረት እና ዝግጁነት መናገራቸውን ገልጸዋል።
በሀገር ውስጥ የተፈጠሩ ችግሮችን በኢትዮጵያ መር በአፍሪካ ድጋፍ ለመፍታት እየተሠራ መሆኑን አቶ ደመቀ መናገራቸውን ቃል-አቀባዩ አስረድተዋል።
የአፍሪካ ሕብረት ኢትዮጵያ ባካሔደችው ስድስተኛው ሀገረ አቀፍ ምርጫ ታዛቢዎችን በመላኩ ምሥጋና ማቅረባቸውንና ምርጫውም ፍትሐዊ እና አሳታፊ እንደነበር መግለጻቸውንም አብራርተዋል።
አቶ ደመቀ ከመደበኛው የአስፈፃሚዎች ስብሰባ ጎን ለጎንም የሁለትዮሽ ውይይት እያካሔዱ መሆናቸውን አምባሳደር ዲና ተናግረዋል ።
39ኛው የአፍሪካ ሕብረት አስፈፃሚዎች ስብሰባ ከሰዓት ውሎውም ሁለት ኮሚሽነሮችን፣ የፓን አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንት ምርጫ እንዲሁም አፍሪካ በዓለም አቀፍ ተቋማት የሥራ ኃላፊነት የምታወዳድራቸውን ዕጩዎች ምርጫ ላይ ይወያያል።
ዘጋቢ:–በለጠ ታረቀኝ–አፍሪካ ሕብረት
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“ኢትዮጵያ ከዘላቂ ጥቅሟ አንጻር የራሷን አማራጭ በመጠቀም የተከፈተባትን ዘመቻ በአሸናፊነት ማጠናቀቅ ይጠበቅባታል” በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር
Next article“ወቀሳም ሆነ ድጋፍ በአመክንዮ ሊሆን ግድ ይላል”