
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) መንግሥት ለሕዝብ የገባውን ቃል ወደ መሬት ሊያወርደው እንደሚገባና የተፎካካሪ ፓርቲዎች በተለያዩ የመንግሥት ኃላፊነቶች ውስጥ መካተት ተስፋ ሰጪ መሆኑን መጋቤ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁ ተናግረዋል።
መጋቤ ሀዲስ እሸቱ እንደተናገሩት መንግሥት ለሕዝብ የገባውን ቃል ወደ መሬት ሊያወርደው ይገባል።
መጋቤ ሀዲስ እሸቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲሁም የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በበዓለ ሲመቱ ወቅት ያደረጉት ንግግር መልካም እንደሆነ ጠቅሰው ቃላቸውን ወደ መሬት እንዲያወርዱ ጠይቀዋል።
እንደ መጋቤ ሀዲስ ንግግር፤ ፓርላማ ላይ የሚደረጉ ንግግሮች መሬት ላይ እስከ ቀበሌ ድረስ መፈፀም ካልቻሉ ብዙ ትርጉም የለውም፤ ቃላቸው በተግባር ላይ ከዋለ ግን ብዙ ለውጦችን ማምጣት ይቻላል፡፡
መጋቤ ሀዲስ እሸቱ የኛን ሀገር ዴሞክራሲ በአውሮፓ ልክ ተቀዶ እንዲሰፋ መጠበቅ አያስፈልግም፤ ጅምሩ ጥሩ ነው፤ የተፎካካሪ ፓርቲዎች በተለያዩ የመንግሥት ኃላፊነቶች ውስጥ መካተት ተስፋ ሰጪ ነው ሲሉም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ባለችበት ሁኔታ ለተፎካካሪ ፓርቲዎቹ እድል መሰጠት እንደ ቀላል የሚታይ አይደለም ያሉት መጋቢ ሀዲስ እሸቱ ‹‹ ተግባሩን ለሀገር ጥሩ እንደሚመኝ አማኝ ሰው የጥሩ ነገር ምልክት ነው ብዬ አስባለሁ ››በማለት ገልጸዋል። ዘገባው የኢፕድ ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ