
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 02/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በባህሬን የኢፌዴሪ ቆንስላ ጄነራል ጽሕፈት ቤት መሪ አምባሳደር ጀማል በከር ከባህሬን የገንዘብና የብሔራዊ ኢኮኖሚ ሚኒስትር ሼክ ሰሊማን ቢን ከልፋ አልካልፋ ጋር የሁለትዮች የኢኮኖሚ፣ የኢንቨስትመንት፣ የንግድ እንዲሁም ሁሉን አቃፍ ትብብር ለማጠናከር ውይይት አድርገዋል፡፡
በዚህ ወቅት አምባሳደር ጀማል በከር ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን ሀገራዊ ለውጥ ከመካከለኛው ምሥራቅ ጋር ያለን ትብብር ለማጠናከር የሚረዳ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የኢኮኖሚ ፕሮግራም ነድፋ እየሠራች ነው፤ በተለይም የኢኮኖሚ ፈተናዎችን በመቋቋም የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ማነቆ የሆኑትን የሕግና የአሠራር ሁኔታዎችን በመፈተሽ ለኢንቨስተሮች ምችሁ ሁኔታ ለመፍጠር እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሩ ሼክ ሰሊማን ቢን ከልፋ አልካልፋ በኢትዮጵያ ሕዝብ ይሁንታ ያገኛው ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ምስረታ በጥሩ ሁኔታ በመጠናቃቁ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን ሀገራዊ ለውጥ ሀገሪቷ ጠንካራና ክልላዊ ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ለማጠናከር የሚያስችል በመሆኑ የባህሬን መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር እንደሚያደርግ አንስተዋል፡፡
በተያያዘም የኢትዮጵያ ዜጎች ለባህሬን ኢኮኖሚ እድገትና ቀጣይነት እያበረከቱ ያለውን ሚና አድንቀው ምስጋና አቅርበዋል፡፡ መረጃው የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ