
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 02/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው ትህነግ በዜጎች ላይ ግፍ በመፈጸም የፖለቲካ ስልጣኑን የመያዝ አደገኛ ተግባሩን መቀጠሉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ቡድኑ ወሯቸው በነበሩ በጎንደርና በሰሜን ወሎ አካባቢዎች በንጹሃን ወገኖች ላይ ግድያ በመፈጸም ለአማራ ሕዝብ ያለውን ጠላትነት በድጋሚ አረጋግጧል ብሏል ሚኒስቴሩ።
አሸባሪው ትህነግ የብዙ ቤተሰቦችን ሕይወት ለማበላሸት ያለመ ቡድን መሆኑን ይዟቸው በነበሩት አካባቢዎች የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ ነው ያለው።
በቅርቡ ተይዘው በነበሩ አካባቢዎች የነበሩ አርሶ አደሮች እንደገለጹትም የአሸባሪው ትህነግ ወታደሮችና ተባባሪዎቻቸው የአርሶ ደሩን ሰብልና ሌሎች ንብረቶች ዘርፈዋል፡፡
ከዚህ የከፋው ደግሞ የገበሬዎችን የተከማቸ ምግብ መውሰዱና ማውደሙ ነው ብሏል ሚኒስቴሩ ባወጣው መረጃ።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ