“የሕዝቦችን መቀራረብ በሚያጎለብቱ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተድርጎ ይሠራል” የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር

95
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 02/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር ከቀድሞው የምክር ቤቱ አፈ-ጉባዔ አቶ አደም ፋራህ ጋር በምክር ቤቱ ሲከናወኑ በቆዩ ጉዳዮችና በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ዋና ዋና አጀንዳዎች ዙሪያ ተወያይተዋል።
በውይይቱ ላይም የፌዴሬሽን ምክር ቤት በቀጣይ በግጭት አፈታትና የሕዝቦችን መቀራረብ በሚያጎለብቱ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሠራ አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ገልጸዋል።
በዉይይቱ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ዛራ ሁሙድና የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ወይዘሮ እፅገነት መንግሥቱና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት የማኔጅመንት አባላትም ተገንተዋል። መረጃው የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነትና የኮምዩኒኬሽን ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleከሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የተሰጠ መግለጫ።
Next articleአሸባሪው ትህነግ በሰሜን ወሎና ጎንደር አካባቢዎች ንጹሃንን በመግደል መሠረተ ልማቶችን ማውደሙን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።