
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 01/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአዲሱ መንግሥት ለተሾሙ ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ አመራሮች በአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
በዚህ ስልጠና መክፈቻ ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ባደረጉት ገለጻ፣ አመራሩ በንፁህ እጅና በቅንነት ሀገሩን ማገልገል አለበት ብለዋል።
የኢትዮጵያ ብልጽግና የሚረጋገጠው ኢትዮጵያ ያሏትን ሀብቶች በአግባቡ በማልማት፣ በትጋት በመስራትና በንፁህ እጅና በቅንነት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
አመራሮች ከስለጠናው በኋላም የዓላማ ጽናት በቡድን የመስራት መንፈስና በስልጠናው ያገኙትን ዕውቀት ወደ ተግባር መለወጥ ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡ ዘገባው የኢፕድ ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ