እየተሠራ የሚገኘው ተለዋጭ የዓባይ ወንዝ ድልድይ ግንባታ 41 ነጥብ 1 በመቶ ላይ መድረሱ ተገለጸ።

434
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 01/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ከተማ በቻይና ኮንስትራክሽን ኮምዩኒኬሽን ካምፓኒ እየተሠራ የሚገኘው ተለዋጭ የዓባይ ድልድይ አጠቃላይ ግንባታው 41 ነጥብ 1 በመቶ ላይ መድረሱ ተገለጸ።
የሥራውን ሂደት የአማራ ክልል ርእስ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) እና የሥራ ኀላፊዎች እየጎበኙት ነው።
በ2011 ዓ.ም ግንባታው የተጀመረው ተለዋጭ የዓባይ ድልድይ 43 ሜትር ስፋት እና 380 ሜትር ርዝመት አለው። ግንባታው በአሁኑ ወቅት 69 ነጥብ 1 በመቶ መድረስ የነበረበት ቢሆንም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ፣ የወሰን ማስከበር ችግር እና የግንባታ ቁሳቁስ እጥረት በዕቅዱ መሰረት እንዳሄድ እንዳደረገው ተጠቅሷል። ፕሮጀክቱ ከተጀመረ ሁለት ዓመታት ከሁለት ወራት ሆኖታል፡፡
ዘጋቢ፦ አዳሙ ሽባባው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“ኢትዮጵያ የተለያዩ ፈተናዎችን ተቋቁማ ጸንታ የቀጠለችው ኢትዮጵያውያን ለሰላም ባላቸው ጽኑ ፍላጎት ነው” የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለም
Next articleበአዲሱ መንግሥት ለተሾሙ ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና እየተሰጠ ነው።