❝አሸባሪው የህወሓት ቡድን የአደገኛ ወንጀለኞች፣ ጨቋኞች እና ውሸታሞች ስብስብ መሆኑን አውቃለሁ❞ አና ጎሜዝ

491

መስከረም 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ እንደነበረው ሰው አሸባሪው የህወሓት ቡድን የአደገኛ ወንጀለኞች፣ ጨቋኞች እና ውሸታሞች ስብስብ መሆኑን አውቃለሁ ሲሉ የቀድሞ የአውሮፓ ሕብረት ፓርላማ አባል አና ጎሜዝ ገለጹ።

አና ጎሜዝ በ1997 ዓ.ም ኢትዮጵያ ያካሄደችውን አጠቃላይ ሀገራዊ ምርጫ ለመታዘብ የመጣው የአውሮፓ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ ነበሩ።

በወቅቱ አፋኝ በነበረው በህወሓት የበላይነት የሚመራው መንግሥት ምርጫው ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሐዊ እና ተዓማኒ እንዳይሆን በማድረጉ አና ጎሜዝ ሲያብጠለጥሉት ቆይተዋል።

አና ጎሜዝ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የሚያደርገውን ተደጋጋሚ ጫና በመቃወም ለድርጅቱ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እና ለግብረሰናይ ድርጅት አመራሮች በትዊተር መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዚሁ መልዕክታቸው በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ እና ልምድ እንደነበረው ሰው የአሸባሪው ህወሓት ቡድን የአደገኛ ወንጀለኞች፣ ጨቋኞች እና ውሸታሞች ስብስብ ነው ሲሉ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የጸጥታው ምክር ቤት እና የሰብዓዊ ድጋፍ አቅራቢ ድርጅቶች ኢትዮጵያ ላይ የሚነዙት ያልተገባ ወቀሳ ነባራዊ ሁኔታን ያላገናዘበ ነው በሚል በርካቶች እየተቃወሙት ይገኛሉ።

በኢትዮጵያ ከተልዕኳቸው ውጪ ሲንቀሳቀሱ ከሀገር እንዲወጡ የተደረጉ የመንግሥታቱ ድርጅት ሠራተኞች ለአሸባሪው ቡድን የተለያየ ድጋፍ ሲያቀርቡ የነበሩ መሆናቸው ተጠቅሷል።

የአሁኑ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ኢትዮጵያ ፋሽስቱ የኢጣሊያ መንግሥት ጸብ አጫሪነቱን እንዲያቆም እና የሀገሯን ሉዓላዊነት እንዲያከብር ለ’ሊግ ኦፍ ኔሽንስ’ እአአ 1935 ያቀረበችውን አቤቱታ ወደጎን በማለት ለኢጣሊያ ይሁንታ መስጠቱ ይታወሳል።

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ሕጎችን መነሻ በማድረግ ለአሸባሪው ቡድን ድጋፍ ያደረጉ የተመድ ተወካዮች ላይ እርምጃ ብትወስድም ፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት እውነታውን ባለመቀበል ኢትዮጵያ ላይ ፊቱን ማዞሩ ”ታሪክ ራሱን ደገመ ” የሚያስብል አቋም እንዲይዝ አድርጎታል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleአዲስ የተመሰረተው መንግሥት አሸባሪው የትህነግ ቡድን በአጭር ጊዜ በመደምሰስ የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ማቋቋም እንደሚገባው የሁመራ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
Next articleኢትዮጵያን በብዙው የመሰለ የሀገር መከላከያ ሠራዊት!