
ሁመራ፡ መስከረም 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲዎችን አሳትፎ አዲስ የተመሰረተው መንግሥት የሀገርን አንድነት በማስጠበቅ እና አሸባሪውን የትህነግ ቡድን በአጭር ጊዜ በመደምሰስ የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ እንዲያቋቁም ጠይቀዋል። በአሸባሪው ቡድን ወረራ ምክንያት የወደሙ አካባቢዎች እንዲለሙ መሥራት ይገባዋል ነው ያሉት።
የሁመራ ከተማ ነዋሪው ወጣት ጠገናው አሸናፊ አዲስ የተመሰረተው መንግሥት ተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲዎችን ማሳተፉ የኢትዮጵያን አንድነት ለማስቀጠል እንደሚያግዝ ያለውን እምነት ገልጿል።
አሸባሪው ቡድን በመደምሰስ የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ማቋቋም ከአዲሱ መንግሥት የሚጠበቅ ተግባር ነው ብሏል።
ወጣት የኃላሸት አድማሱ በበኩሉ “የምዕራባውያን ጫና አያስፈራንም፤ አዲስ የተመሰረተው መንግሥት ኢትዮጵያ ያጋጠማትን ፈተና በድል እንድትወጣ በኀላፊነት እንደሚሠራ ሙሉ እምነት አለኝ” ነው ያለው።
ኢትዮጵያ የያዘችውን የእውነት መንገድ ያልተረዱ ለጥቅማቸው ሲሉ ለአሸባሪው የትህነግ ቡድን ድጋፍ እያደረጉ ያሉ አካላትን በጋራ መመከት እንደሚገባ ገልጿል።
ወጣት የኃላ እሸት ኢትዮጵያ በታሪኳ የተከሰቱትን የውጭ ወራሪና የሀገር ውስጥ ባንዳዎችን ድባቅ እንደመታች ሁሉ አሁንም በነፃነት በመረጠችው መንግሥት ሉዓላዊነቷን አስከብራ ትኖራለች ብሏል።
ወጣት አሸናፊ ለማ የኢኮኖሚ አሻጥር በመሥራት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የከፋ ችግር ለመፍጠር እየተንቀሳቀሱ ያሉትን የውስጥ እና የውጭ አካላትን በመቆጣጠር መንግሥት እየታየ ያለውን የዋጋ ንረት እልባት ሊሰጠው እንደሚገባም ገልጿል።
ዘጋቢ፡- ያየህ ፈንቴ- ከሁመራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m