የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ አቶ በለጠ ሞላ ከቀድሞው ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ ጋር የሥራ ርክክብ አድርገዋል።

454

አዲስ አበባ: መስከረም 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የመከላከያ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ዶክተር አብርሃም በላይ በሚኒስቴሩ በነበራቸው ቆይታ ከጎናቸው የነበሩትን ኹሉ አመስግነው ለአዲሱ ሚኒስትርም ድጋፋቸውን እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

ዶክተር አብርሃም ከተቋሙ ጋር በጋራ እንደሚሠሩም ገልጸዋል።

ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በጋራ የመሥራት ምዕራፉ እንደ ሀገር ትልቅ ርምጃ የሚያስኬድ መሆኑንም ተናግረዋል።

አዲሱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር አቶ በለጠ ሞላ በበኩላቸው በተጀመሩ ሥራዎች ላይ ተጨባጭ ተግባራትን በማከናወን ለሀገራችን የምንችለውን ኹሉ በጋራ ለማበርከት እንሠራለን ብለዋል።

ተቋሙ በሁሉም ዘርፍ የጠነከረና የተቋም ግንባታ ተምሳሌት እንዲኾን ይሠራል ነው ያሉት።

ተፎካካሪ ፓርቲዎች ለሀገር ያላቸው የሐሳብና የተግባር አበርክቶ እንዲወጡ እድል የሰጠ ምዕራፍ መሆኑንም ገልጸዋል። ተቋሙ ሀገር ብዙ ነገር የምትጠብቅበት ስለኾነ ከሁሉም ጋር ተባብረን የሚጠበቅብንን እንወጣለን ብለዋል።

ዘጋቢ:- ዘመኑ ታደለ – ከአዲስ አበባ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Previous articleኳታር ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር) የደስታ መግለጫ ላከች።
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ለከፍተኛ የመንግስት ሃላፊነት ቦታዎች ሹመቶች ሰጡ:-