
ባሕር ዳር፡ መስከረም 28/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኳታሩ አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አልታኒ፣ ምክትል አሚር ሼክ አብዱላህ ቢን ሃማድ አል ታኒ እና የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር እና የሀገር ውስጥ ሚኒስትሩ ሼክ ካሊድ ቢን ካሊፋ ቢን አብዱላዚዝ አልታኒ ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው የደስታ መግለጫ ልከዋል።
መሪዎቹ በላኩት የደስታ መግለጫ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ዶክተር ዐቢይ ለሀገራቸው እና ሕዝባቸው ልማት እና ብልፅግና የተሻለ ስኬት እንዲያስመዘግቡ መልካም ምኞታቸውንም ገልፀዋል። መረጃው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m