
ባሕር ዳር፡ መስከረም 19/2012 ዓ/ም (አብመድ) በሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌትና አለቃቀቅ ዙሪያ የተቋቋመው የሦስትዮሽ ብሔራዊ ገለልተኛ የሳይንሳዊ ጥናት ቡድን እየተወያዬ ነው፡፡
በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌትና አለቃቀቅ ዙሪያ የተቋቋመው የኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና የግብጽ የሦስትዮሽ ብሔራዊ ገለልተኛ የሳይንሳዊ ጥናት ቡድን አምስተኛ ስብስባውን በካርቱም – ሱዳን ማካሄድ ጀምሯል።
አንደ ኤፍቢሲ ዘገባ ቡድኑ ቀጣይ በካርቱም በሚካሄደው የሦስቱ ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ሪፖርት እንደሚያቀርብ ይጠበቃል።
የጥናት ቡድኑ መስከረም 15 እና16/2019 (እ.አ.አ) በካይሮ በተደረገው ስብሰባ የሦስቱ ሀገራት የውሃ ሚኒስትሮች በተለዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይተው ነበር፡፡