ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ።

212
መስከረም 28/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመመረጣቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ የሩስያና የኢትዮጵያ ግንኙነት ታሪካዊና በሁለትዮሽ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በቀጣይ የሥራ ዘመናቸው የሁለቱ ሀገራት ሕዝቦች ከሀገራቱ የጋራ ትብብር በልማት ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ ሥራዎችን ያከናውናሉ ብለው እንደሚያምኑም ፕሬዚዳንት ፑቲን አመላክተዋል።
በአፍሪካ ጸጥታና መረጋጋት ላይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የተጠናከረ ሥራ እንደሚሠሩም ያላቸውን እምነት መግለጻቸውን በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበአሸባሪው የትህነግ ቡድን የወደሙ የትምህርት ግብዓቶችን በማሟላት የመማር ማስተማር ሂደቱን ማስጀመሩን የሁመራ ከተማ ትምህርት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
Next articleተቋማት በሶሻል ሚዲያ አጠቃቀም ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ አሳሰበ።